በዩክሬን ዙሪያ ሩሲያ እና ቱርክ ውይይታቸው ምን ነበር ?

Date:

ዛሬ የቱርኩ ፕሬዝደንት ሬሴፕ ጣይብ ኤርዶጋን እና የሩሲያው ፕሬዝደንት ቭላዲሚር ፑቲን በስልክ ተነጋገረዋል። ሁለቱ መሪዎች በዩክሬን ጦርነት ዙሪያ ስላሉት ሁኔታዎች ተወያይተዋል።

የቱርክ ፕሬዝዳንት ጽህፈት ቤት ባወጣው መግለጫ መሠረት፣ ሬሴፕ ጣይብ ኤርዶጋን ለሩሲያው አቻቸው “የሰላም ሂደቱን ሁኔታ በቅርበት እየተከታተለ መሆኑን፣ ቱርክ ከጦርነቱ መጀመሪያ ጀምሮ ፍትሃዊ ሰላም ለማምጣት ቅን ጥረት ስታደርግ እንደቆየች እና ሁሉም አካላት በሚሳተፉበት ዘላቂ ሰላም ለመመስረት ያለመ አቋምን እንደምትደግፍ” ገልጸዋል።

የሩሲያው ፕሬዝደንት በኢስታንቡል የተካሄደውን የሩሲያ እና የዩክሬን ልዑካን ስብሰባ በመጥቀስ፣ ቱርክ የሰላም ንግግሩን በማስተናገዷ እና ለሚያደርገው ጥረት ጣይብ ኤርዶጋንን አመስግነዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ምንገድ ላይ

(በእውቀቱ ስዩም) በቀደም ከሆነ ቦታ ተነስቼ ወደ አልሆነ ቦታ ስራመድ...

ብፁዕ ካርዲናል አቡነ ብርሃነ ኢየሱስ በጡረታ ከኃላፊነታቸው ተሰናበቱ

የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያንና የአዲስ አበባ አገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ...

አትሌት ጉዳፍ ጸጋዬ አዲስ መግለጫ አወጣች

ታዋቂዋ አትሌት ጉዳፍ ጸጋዬ ለስፖርት ወዳጆችና ለደጋፊዎቿ ወቅታዊ መረጃ...