“ዝክረ ዶ/ር ደረጀ ዘለቀ”የመታሰቢያ ፕሮግራም የፊታችን ቅዳሜ ይካሄዳል። አንጋፋው ኢትዮጵያዊው ምሁር ዶ/ር ደረጀ ዘለቀ ከዚህ ዓለም የተለየበትን አንደኛ አመት ምክንያት በማድረግ፣ “ዝክረ ዶ/ር ደረጄ ዘለቀ” በሚል ርዕስ የመታሰቢያ ፕሮግራም ሊካሄድ ነዉ።
በዚህ የመታሰቢያ ፕሮግራም ላይ የዶ/ር ደረጀ ዘለቀን የተለያዩ የህይወት ገፅታዎችና ምዕራፎች የሚያስታዉሱ ዝግጅቶች ይቀርባሉ፡፡
ቀን:- ቅዳሜ ነሐሴ 17 ቀን 2017 ዓ.ም
ሰዓት:- ከጠዋቱ 3:00
ቦታ:- አራት ኪሎ ግንፍሌ ድልድይ ስር በሚገኝው አዲሱ “አማራጭ የማሰቢያ ስፋራ” አዳራሽ
