ስዊዘርላንድ በፀሐይ ኃይል የሚሰራ አውሮፕላን

Date:

ስዊዘርላንድ በፀሐይ ኃይል ብቻ የሚሰራ አውሮፕላን ከ31,000 ጫማ በላይ ከፍታ በማብረር በአለም ታሪክ አዲስ ክብረወሰን ማስመዝገቧ ተገለጸ።

“ሶላርስትራቶስ” የተሰኘው ይህ ቀላል ክብደት ያለው አውሮፕላን፣ በንጹህ የፀሐይ ኃይል ብቻ የሚሰራ ሲሆን፣ ምንም አይነት ልቀት ሳያመነጭ እስከ 9,521 ሜትር (31,237 ጫማ) ከፍታ መድረስ ችሏል ነው የተባለው።

ይህ ታሪካዊ በረራ ዘላቂነት ያለው የአቪዬሽን ቴክኖሎጂ ምን ያህል እድገት እያሳየ እንደሆነ የሚያሳይ ትልቅ ምዕራፍ ነው ተብሎለታል።

የፕሮጀክቱ ዋና አብራሪ የሆኑት ራፋኤል ዶምጃን፣ አውሮፕላኑን ከስዊዘርላንድ ሲዮን አውሮፕላን ማረፊያ በማንሳት ይህንን የላቀ ብቃት ማሳየታቸው ተነግሯል።

አውሮፕላኑ በፀሐይ ኃይል እና በተፈጥሯዊ የአየር ሞገዶች ብቻ የሚበር መሆኑ፣ በአካባቢ ላይ ጉዳት የማያደርስ በረራ ምን ያህል ሊሳካ እንደሚችል ያሳያል ነው የተባለው።

ይህ ስኬት ንጹህ እና ለወደፊት ወደ ሰማይ ጠፈር ለመድረስ ለሚደረጉ የኤሮኖቲክስ ተልዕኮዎች አዲስ መንገድ የሚከፍት ነው ተብሏል።

የዓለም የአየር ስፖርት ፌዴሬሽን ይህንን መረጃ በይፋ ለማረጋገጥ ምርመራ እያደረገ ነው ተብሏል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ምንገድ ላይ

(በእውቀቱ ስዩም) በቀደም ከሆነ ቦታ ተነስቼ ወደ አልሆነ ቦታ ስራመድ...

ብፁዕ ካርዲናል አቡነ ብርሃነ ኢየሱስ በጡረታ ከኃላፊነታቸው ተሰናበቱ

የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያንና የአዲስ አበባ አገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ...

አትሌት ጉዳፍ ጸጋዬ አዲስ መግለጫ አወጣች

ታዋቂዋ አትሌት ጉዳፍ ጸጋዬ ለስፖርት ወዳጆችና ለደጋፊዎቿ ወቅታዊ መረጃ...