በኦሞ ወንዝና በቱርካና ሃይቅ መሙላት የኦሞራቴ ከተማ ታሪክ ልትሆን ተቃርባለች

Date:

የዳሰነች ወረዳ ዋና ከተማ የሆነችው የኦሞራቴ ከተማ ከዓመት ዓመት በቱርካና ሃይቅ እና በኦሞ ወንዝ መሙላት ምክንያት የመዋጥ ስጋት እንዳለባት ሲነገር ቆይቷል፡፡

ከተማዋን የተጠጋት ውሃ ዘልቆ እንዳይገባ ጊዜያዊ መከላከያ ግድብ ቢሰራም ውሃው በከፍተኛ መጠን እየመጣ በመሆቡ ግድቡን ጥሶ ከተማዋን እንዳያጥለቀልቃት ስጋት ውስጥ ነን ያሉን የዞኑ አደጋ ስጋት ቢሮ ምክትል ሃላፊ ኞክ ኛንጋ ሞሮኜ ናቸው፡፡

በ2017 ዓ/ም መጀመሪያ የመስከረም ወር አካባቢ በአቅራቢያ ያሉ የደቡብ ኦሞ ወረዳዎችን ውጦ በማስቀረት ወደ ዋና ከተማዋ ኦሞራቴ ለመድረስ የ1.5 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የነበረው የቱርካና ሃይቅ ሙላት አሁን በጥቂት መቶ ሜትሮች ላይ ነው ያለው ተብሏል፡፡

ይህ ሁሉ ሲሆን ከፌድራሉ መንግስት ድጋፍ አልጠየቃችሁም ወይ?ያልናቸው ምክትል ሃላፊው፤ ለፌዴራሉ መንግስት በተለይ ለአደጋ ስጋት መስሪያ ቤት በተደጋጋሚ አሳውቀናል፤ ነዋሪውም ጠቅላይ ሚኒስትሩ መጥተው ያሉበትን ችግር እንዲያዩ ጥሪ አድርጓል ነገር ግን ይህ ነው የሚባል ምላሽ አላገኘንም ብለዋል፡፡

ባለፈው ዓመት በነበረው መጥለቅለቅ ከአካባቢያቸው የለቀቁ ከ81,000 በላይ ነዋሪዎችን ደረቅ በሆኑ ቦታዎች አስፍረን ድጋፍ እያደረግንላቸው ነው ሲሉም አስረድተዋል፡፡

የውሃው ሙላት በዚህ ቀጥሎ የተሰራውን መገደቢያ የሚያፈርስ ከሆነ በመቶ ሺህዎች የሚቆጠረውን የኦሞራቴ ከተማ ነዋሪ ወደ ሌላ ቦታ ለማስፈር እየተዘጋጁ መሆኑን ከሃላፊው ሰምተናል፡፡

የፌድራሉ መንግስት ችግሩን እንዲመለከተውና መፍትሄ እንዲሰጣቸው የጠየቁት ሃላፊው እያደረግን ያለነው ሙከራ ከአቅማችን በላይ እየሆነ ነው አቅማችን ተሟጧል ከተማችን ሳትጠፋ ድረሱልን ብለዋል፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የተፈናቀሉ ዜጎች በተጠለሉበት አካባቢ በቋሚነት መኖር የሚያስችላቸው 

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን የዳሰነች ወረዳ ከበኦሞ...

ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ 11ኛውን የኃይሌ ሆቴልና ሪዞርት በደብረ ብርሃን ከተማ አስመረቀ

ታዋቂው አትሌትና ባለሀብት ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ፣ በደብረ ብርሃን ከተማ...

በኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር የተዘጋጀው የመጀመሪያው አህጉራዊ የሪል ስቴት ኤግዘቢሽን ተከፈተ

በኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር አዘጋጅነት የመጀመሪያው አህጉራዊ የሪል...

በሊባኖስ እና በእሰራኤል የተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት ተራዘመ

ትራምፕ በሊባኖስ እና በእሰራኤል መካከል የተደረሰው የተኩስ አቁም በሦስት...