የዎላይታ ድቻ ለሲዳማ በስህተት ተሰጥቶ የነበረውን የኢትዮጵያ ዋንጫን ተረክቧል

Date:

የዎላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪና የዎላይታ ድቻ ስፖርት ክለብ የበላይ ጠባቂ ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት ስራ ኃላፊዎች፣ ተጨዋቾች እና ደጋፊዎች በተገኙበት የርክክብ ሥነሥርዓት ተደርጓል።

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ፕሬዚዳንት ኢሳያስ ጅራ ዋንጫውን ለክለቡ በክብር አስረክበዋል።

በወላይታ ድቻ እግር ኳስ ክለብ እና በሲዳማ ቡና እግር ኳስ መካከል በተደረገ የኢትዮጵያ ዋንጫ ፍጻሜ ጨዋታ የሲዳማ አቻው 2 ለ 1 በሆነ ውጤት ያሸነፈ ቢሆንም ተገቢ ያልሆነ ተጫዋች በማሰለፉና በዳኝነት ችግር የዎላይታ ድቻ እግር ኳስ ቡድን 3 ንፁህ ጎል እና 3 ነጥብ በማግኘት አሸናፊ መሆኑን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን መወሰኑን ይታወሳል።

ዋንጫው መጪዉ አርብ ነሓሴ 30/2017 ዓ.ም ወደ ዎላይታ ዞን የሚገባውን የጀግና አቀባበል ለማድረግ ሁሉም ህብረተሰብ ክፍል የስፖርት ጨዋነትን በተላበሰ መልኩ በነቂስ መውጣት እንዳለባቸውም ጥሪ ቀርቧል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አክሊሉ ወንድሞቹ ለንባብ በቃ

በፀሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ የልጅነት ታሪክ ላይ ያተኮረ ለታዳጊዎች...

የኢራን ተፈጥሮአዊ ምሽጎች እና ስትራቴጂካዊ ጥበብ

​ግዮን መጽሔት :- በመካከለኛው ምስራቅ የጂኦ-ፖለቲካ ትኩሳት...

ለአድዋ ድል መታሰቢያ በአሜሪካ ቀን ተሰየመ

በአሜሪካ፣ የፔንሲልቪኒያ ግዛት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የአውሮፓዊያኑ 'መጋቢት...

ኢሎን መስክ የዓለማችን የመጀመሪያው ትሪሊዮነር ሆነ

ኢሎን መስክ የሀብት መጠኑ 1 ትሪሊዮን ዶላር ያለፈ የመጀመሪያው...