የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ በተመድ 80ኛ ጉባዔ ላይ ካደረጓቸው ንግግሮች

Date:

🟠 ዛሬ ላይ የፍልስጤም መንግሥት ምስረታን በተመለከተ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ውሳኔን ለመቅበር የሚደረግ ሙከራን በተግባር እየተጋፈጥን ነው።

🟠 ለፍልስጤም እውቅና በሚሰጥበት ወቅት ምንም ዓይነት ግዛት እንዳይቀር የሚደረጉ ሙከራዎችን ለመከላከል አስቸኳይ እርምጃዎች መወሰድ አለባቸው።

🟠 ሩሲያ ምዕራባውያን የፀጥታው ምክር ቤት ማዕቀቦችን በኢራን ላይ መልሶ እንዲጥል የሚያደርጉትን ሙከራ ተቀባይነት የሌለውና ሕገ-ወጥ አድርጋ ትቆጥረዋለች።

🟠 ሩሲያ የዩክሬን ግጭት መንስኤዎችን ለመፍታት ለድርድር ዝግጁ ነች።

🟠 የሩሲያ ደህንነት እና ቁልፍ ጥቅም በአስተማማኝ ሁኔታ መረጋገጥ አለበት።

🟠 በዩክሬን ግዛቶች የሩሲያውያን እና የሩሲያኛ ተናጋሪ ሕዝቦች መብት ሊመለስ ይገባል።

🟠 ሩሲያ የኔቶ አባል ሀገራትን ለማጥቃት እቅድ የላትም፣ ነገር ግን ለማንኛውም ጥቃት የማያወላዳ አፀፋዊ ምላሽ ትሰጣለች።

🟠 ሞስኮ በቀጣይ የሩሲያ እና አሜሪካ ውይይት የዩክሬን ጉዳይ መፍትሄ እንደሚያገኝ ተስፋ ታደርጋለች።

🟠 ፑቲን በ ‘ኒው ስታርት’ ስምምነት ስር ገደቦችን ለማስቀመጥ ያቀረቡት ሃሳብ፤ የጦር መሳሪያ እሽቅድምድምን ለማስቀረት አስቻይ ሁኔታ ይፈጥራል።

🟠 ሩሲያ የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት መሻሻልን ትደግፋለች፤ ማንም ላይ የተለየ ዘመቻ አታደርግም።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ 11ኛውን የኃይሌ ሆቴልና ሪዞርት በደብረ ብርሃን ከተማ አስመረቀ

ታዋቂው አትሌትና ባለሀብት ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ፣ በደብረ ብርሃን ከተማ...

በኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር የተዘጋጀው የመጀመሪያው አህጉራዊ የሪል ስቴት ኤግዘቢሽን ተከፈተ

በኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር አዘጋጅነት የመጀመሪያው አህጉራዊ የሪል...

በሊባኖስ እና በእሰራኤል የተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት ተራዘመ

ትራምፕ በሊባኖስ እና በእሰራኤል መካከል የተደረሰው የተኩስ አቁም በሦስት...

ከ 50 ሚሊዮን በላይ መራጮች በማንዋልና በዲጂታል ተመዝግበዋል

ከየካቲት 28_መጋቢት 28 የመራጮች ምዝገባ ሲካሄድ እንደነበር ይታወቃል። በተለያዩ ጉዳዮች...