ባንኩ በመጀመሪያ የሥራ ዓመቱ 22.4 ሚሊዮን ብር ወጪ አደረገ

Date:

በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የግል የኢንቨስትመንት ባንክ የሆነው ወጋገን ካፒታል ኢንቨስትመንት ባንክ የ2017 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸሙን ይፋ አድርጓል።

የኢንቨስትመንት ባንኩ 7.9 ሚሊዮን ብር ገቢ ያስመዘገበ ቢሆንም፣በመሠረተ-ልማት ግንባታ ላይ በዋለ ስትራቴጂካዊ ኢንቨስትመንት ሳቢያ፣ ወጪው 22.4 ሚሊዮን ብር መድረሱን አስታውቋል።

የኩባንያው ዋና ስራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ብሩታዊት ዳዊት፣ የፋይናንስ ውጤቱ በመክፈቻ ምዕራፍ የሚጠበቅ ነው ብለዋል።

ትኩረታቸው ፈጣን ትርፍ ላይ ሳይሆን፣ በቋሚ ንብረቶች፣ በሠራተኞች ሥልጠናና ልምድ ባላቸው የውጭ ባለሙያዎች ቅጥር ላይ በመዋዕለ ንዋይ በማፍሰስ “ለዘላቂ እድገት ጠንካራ መሠረት መጣል” ላይ እንደነበር አስረድተዋል። ባንኩ በቀጣዩ የሒሳብ ዓመት ትርፋማ ይሆናል የሚል እምነት እንዳላቸውም ገልጸዋል።

እኤአ በመጋቢት 2025 ዓ.ም. ሥራውን የጀመረው ወጋገን ካፒታል ኢንቨስትመንት ባንክ በአገሪቱ አዲስ በተቋቋመው የፋይናንስ ዘርፍ ወሳኝ ተዋናይ እንደሚሆን ወ/ሮ ብሩታዊት አክለዉ ተናግረዋል።

ከተጀመረ ከሁለት ወራት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ፣ ባንኩ ከባንክ፣ ኢንሹራንስ እና ሪል እስቴት ጨምሮ ከተለያዩ ዘርፎች 15 ደንበኞችን በመሳብ፣ ስድስት የአማካሪነትና የደላላነት ኮንትራቶችን የፈረመ ሲሆን፣ 37 የኢንቨስትመንት አካውንቶችንም መክፈቱን ካፒታል ሰምቷል።

ባንኩ የጀመረው በ385 ሚሊዮን ብር የተከፈለ ካፒታል ሲሆን፣ ጠቅላላ ንብረቱ 387.8 ሚሊዮን ብር እንዲሁም የባለቤትነት ድርሻው 374.8 ሚሊዮን ብር መድረሱን ዓመታዊ ሪፖርቱ ያሳያል።

CapitalNews

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በሆርሙዝ የባህር ወሽመጥ ላይ በከባድ መሳሪያዎች የታገዘ  የተኩስ ልውውጥ ተካሄደ

ለዓለም የንግድ ሰንሰለት እጅግ ስትራቴጂካዊ በሆነው የሆርሙዝ ባህረ ወሽመጥ...

የሲ.ኤን.ኤን መስራች ቴድ ተርነር ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

የዓለማችን ግዙፍ የዜና አውታር ሲኤንኤን መስራች ቴድ ተርነር በ87...

የኢትዮጵያ አጠቃላይ ብድር 51.8 ቢሊዮን ዶላር መድረሱ ይፋ ሆኗል

ኢትዮጵያ  በድጋፍ መልክ ከአሜሪካ በየዓመቱ  በመንግስት በኩል ፈሰስ የሚደረግ...

ከ8 ሺህ በላይ ጥንታዊ የብራና ጽሑፎችን እና ሰነዶችን ወደ ዲጂታል ተቀየሩ

የኢትዮጵያ ቤተ መዛግብት እና ቤተ መጽሐፍት አገልግሎት ከተለያዩ ተቋማት፣...