አዲሱ የቴክኖ ካሞን 40 በካሜራ እና በሌሎች ቴክኖሎጂዎች ከፍ ብሎ 50 ሜጋ ፒክስል የሶኒ ካሜራ ፣8 ሜጋ ፒክስል አልትራ ዋይድ አንግል ካሜራ እንዲሁም የቴክኖ ኤ አይ ቴክኖሎጂዎችን አካቷል።
የቴክኖ ካሞን 40 በተዋወቀበት በአዲስ ኮንቬንሽን ኢንተርናሽናል ሴንተር የሀገሪቱን ባህል፣ ቀለም፣ መልክዓ ምድርን የሚያሳዩ እና ከፍ ባለ ደረጃ የተነሱ ፎቶዎችም ለሁለተኛ ጊዜ ለዕይታ ቀርበዋል።
ፕሮግራሙ ከቦርድ ሴልፎን አዲስ አበባ ጋር በመተባበር በሀረር፣ ድሬዳዋ፣ ቁንዱዶ ተራራ እና አዲስ አበባ የተነሱ 2መቶ50 ፎቶዎችን ለዕይታ በኤግዚቢሽን መልክ ለእይታ የቀረብበት ነው።
በፕሮግራሙ የቴክኖ ምርቶች የሆኑት አዲሱ የቴክኖ ታብሌት ሜጋ ፓድ፣ የተለያዩ የቴክኖ ሞዴል ስልኮች፣ ኤር ፖዶች ፣ስማርት ሰዓቶች፣ ላፕቶፖች እና ሌሎችም ለጎብኚዎች ቀርበው ነበር፡፡
ይህ ፕሮግራም በቴክኖ ካሞን 40 የካሜራ ሌንስ የኢትዮጲያን ልዩ ገፅታ ለማህበረሰቡ ማድረስ እና ማህበረሰቡን ከቴክኖሎጂ ጋር ማስተዋወቅ አላማው ያደረገ ጥምረት ሲሆን፤ ወደፊትም መሰል ፕሮግራሞች ላይ ቴክኖ ኢትዮጵያ እንደሚሰራ አስታዉቋል፡፡በፕሮግራሙ ከፍተኛ የመንግስት ሃላፊዎች፣ ፎቶግራፈሮች፣ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች፣ የቴክኖሎጂ አድናቂዎች እና ሌሎችም ተሳታፊ ተገኝተዋል።
