የእጅ አሻራችን ስለ እኛ እውነቱን ያናገራል ፡፡ አይዋሸም፡፡ የእግር አሻራችን ሰለ እኛ እውነቱን ይናገራል ፡፡ አይዋሸም፡፡የእናቴ እጆችን ስመለከተው አንዳንዱ ቆስላል፤ አንዳንዱ ጠቁራል ፡፡ አንዳንዱ ሻካራ ሆናል፡፡ብዙ ጊዜ ባዝሊን ትቀባዋለች፡፡ ይህ የእናቴ እጅ አሻራ ስለ እናቴ የሚናገረው ነገር አለ፡፡ የእናቴ የጠቆሩ እጆች፤ የተጠበሱ እጆች፤ የድሙ እጆች፤ የቆስሉ እጆች፤ ስለ እናቴ እውነቱን ይናገራሉ፡፡
ይህም እናቴ ታታሪ ስራተኛ መሆናን ይናገራል፡፡ ጎበዝ ስራተኛ መሆናን ይናገራል፤ብርቱ ስራተኛ መሆናን ይናገራሉ፡፡የእናቴ ጠባሳ እጅ ስለ እናቴ ትጉነት ነው የሚናገረው፡፡
የእጅ አሻራችን ስለ እኛ እውነቱን ያናገራል
የእኛ እጅ ስለ እኛ ምን ይናገራል? የእናንተ እጅ ስለ እናንተ ምን ይናገራል? የአንተ እጅ ስለ አንተ ምን ይናገራል? የአንቺ እጅ ስለ አንቺ ምን ይናገራል?
እጃችን መጥፎም ሆነ መልካም ማድረግ ይችላል
እጃችሁ ማንን ነካበት? ማንን እረዳበት? እጃችሁ ማንን ወጋበት? እጃችሁ ማንን አከመበት? እጃችሁ ለማን ተቆረሰበት? እጃችሁ ማንን መረቀበት? እጃችሁ ምን አይነት ድልድይ ሰራ? እጃችሁ ምን አፈረሰ? እጃችሁ ማንን ሰብረ? እጃችሁ ማን ላይ ምን አለ?
እጃችንን ሁል ጊዜ ሌሎችን ለመረዳት እናድረገው፡፡ እጃችንን ሁል ጊዜ ሌሎችን ለማቅፍ እናድርገው፡፡ እጃችንን ሁል ጊዜ ሌሎችን ለማበራታት እናድርገው፡፡ እጃችንን ሁል ጊዜ ሌሎችን ለመደገፍ እናድርገው፤ እጃችንን ሁል ጊዜ ሰውን ለማገዝ እንጠቀምበት፡፡ እጃችንን ሁል ጊዜ ሰውን ለመግደል አንጠቀምበት፡፡ እጃችንን ሁል ጊዜ ሰውን ለመስበር አንጠቀምበት፡፡የእየሱስ እጅ ስለ እየሱሱ ይናጋራለ፡፡ የእየሱስ የቆሰለው እጆች ስለ እየሱስ እውነቱን ይናጋራሉ፡፡
አንድ ወቅት ቅዱስ አውግስጢኖስን በፍትወትና በዝሙት ህይወቱ የሚያውቁት አንድ ቀን አገኘትና የባለፈውን ማንነቱን እያነሱ ሊወግሩት ና ሊያሸማቅቁት ሲሞክሩ” ያ ሰው አሁን እኔ አይደልሁም” አላቸው፡፡ በእርግጥ ይህ የሄሮድስ ሀሳብ ና መንፈስ ለሁለት ዓመት የቤተ ልሔም ሕፃናትም አልራራም፡፡
አንዳንድ እንሰሳ እንኳ ሲሞት ቆዳውን ትቶ ይሞታል ፣ እኛ ለትውልድ ምን ትተን እንሄድ ይሆን?
ክፋት? ምቀኝነት? ጥላቻ?
