ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ሶማሊያ ገብተዋል

Date:

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ሞቃዲሾ አዳን አብዱል አለማቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሀሙድ አቀባበል እንዳደረጉላቸው የሶማሊያ የዜና ምንጮች ዘግበዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ በቱርክ አደራዳሪነት ውጥረት ለማርገብ ከተስማሙ ወዲህ ሞቃዲሾ ሲገቡ የዛሬው ለመጀመሪያ ጊዜ ነው።

በቆይታቸውም ከፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሃሙድ ጋር እንደሚመክሩ ይጠበቃል።

ኢትዮጵያ ባለፈው አመት ሶማሊያ እንደ ግዛቷ አካል ከምትቆጥራት ሶማሊላንድ ጋር የተፈራረመችውን የመግባቢያ ሰነድ የአዲስ አበባ እና ሞቃዲሾን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ማሻከሩ ይታወሳል።

ከአንድ አመት በላይ የዘለቀው ውጥረት በቱርክ አደራዳሪነት የሁለቱ ሀገራት መሪዎች በአንካራ ፊትለፊት ከተገናኙ በኋላ መርገቡም አይዘነጋም።

በአንካራው ስምምነት መሰረትም የሁለቱ ሀገራት ባለስልጣናት ባለፉት ወራት በሞቃዲሾ እና በአዲስ አበባ በመገናኘት ንግግር ሲያደርጉ ቆይተዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አክሊሉ ወንድሞቹ ለንባብ በቃ

በፀሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ የልጅነት ታሪክ ላይ ያተኮረ ለታዳጊዎች...

የኢራን ተፈጥሮአዊ ምሽጎች እና ስትራቴጂካዊ ጥበብ

​ግዮን መጽሔት :- በመካከለኛው ምስራቅ የጂኦ-ፖለቲካ ትኩሳት...

ለአድዋ ድል መታሰቢያ በአሜሪካ ቀን ተሰየመ

በአሜሪካ፣ የፔንሲልቪኒያ ግዛት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የአውሮፓዊያኑ 'መጋቢት...

ኢሎን መስክ የዓለማችን የመጀመሪያው ትሪሊዮነር ሆነ

ኢሎን መስክ የሀብት መጠኑ 1 ትሪሊዮን ዶላር ያለፈ የመጀመሪያው...