የትግራይ ሙሁራን እና ባለሙያዎች ማሕበር (GSTS) በትግራይ ያንዣበበው የጦርነት ዳመና በሰላማዊ መንገድ እንዲፈታ ጥሪ አቀረበ።
ማሕበሩ ባወጣው አስቸኳይ መግለጫ ” የትግራይ ሕዝብ ዋናው ፍላጎት ሰላምና ሰላም ብቻ ነው ” ብሏል።
ከጫፍ እስከጫፍ ያለው የትግራይ ህዝብ ጦርነትና የጦርነት ወሬ መስማት አይፈልግም ያለው ማሕበሩ ” ህወሓት እና አንዳንድ የጦር ጀነራሎች የፕሪቶሪያ የተኩስ አቁም ስምምነትን መሰረት በማድረግ ነገሮችን በሰላማዊ መንገድ ከመፍታት ይልቅ ትግራይን ወደ ሌላ ዙር ጦርነት ለማስገባት እየፎከሩና የጦርነት ዝግጅት እያደረጉ ነው ” ብሏል።
” ሕዝብን የሚመራ አካል ጦርነት ለማስቀረት ይጥራል እንጂ ወደ ጦርነት የሚያመሩ ንግግሮችና ተግባራትን መፈጸም የለበትም ” በማለትም የክልሉን ጊዚያዊ አስተዳደርም ወቅሷል።
አሁን በአካባቢው እያንዣበበ ያለውን የጦርነት ድባብን ለማስቀረት ሕዝቡ፣ በትግራይ ሐይሎችና በዓፋር ያሉ የታጠቁ ሐይሎች እንዲሁም የዳያስፖራው ማሕበረሰብ ለሰላም መቆም እንዳለባቸው አሳስቧል።
የማሕበሩ የአመራር አባል የሆኑት ዶ/ር ገብረኪዳን ገ/ስላሴ ለዶቼ ቨለ ሬድዮ በሰጡት ማብራሪያ ምን አሉ ?
” የትግራይ ሕዝብ ፍላጎት ሰላም ነው።
ሁለተኛ ጦርነት እንዳይመጣ እንጸልያለን።
ሆኖም ግን እንደዛ አይነት ጥሪ (የጦርነት ጥሪ) የሚያደርጉ በሁሉም ወገን ካሉ ወጣቱ የዚህ ሰለባ እንዳይሆን፤ ሕዝባችንም በሰራዊት ያሉም አንዱ ሀራ መሬት የሚባል አለ፤ ሌላው ቲዲኤፍ ትግራይ ውስጥ ያለው በመካከላቸው ምንም ወደ ግጭት የሚወስዳቸው ነገር ስለሌለ ወደዛ እንዳይሄዱ፤ እና ወጣቱ የጦርነት ሰለባ እንዳይሆን ጥሪ አድርገናል።
ሕዝቡ ‘ እምቢ ለጦርነት ‘ ማለት አለበት።
ያለው ልዩነት የፖለቲካ ልዩነት ነው። በፖለቲካ ውይይት እንዲፈቱት ነው የምንጠይቀው። ከዚህ በተጨማሪ ግን ህብረተሰቡ እራሱ ሕብረተሰቡ ፖለቲከኞች በሚፈጥሩት ግጭት ወደ ጦርነት እንዳይገባ የራሱን ተፅዕኖ ማድረግ አለበት። ለጦርነት ‘ እምቢ ‘ ማለት አለበት። ” ብለዋል።
@tikvahethiopia
