Date:

የአል-ነጃሺ መስጅድ ቅርስ ጥገና በመጋቢት ወር ይጠናቀቃል ተባለ።

መስከረም ወር ላይ  የቅርሱ የእድሳት ስራዉ የተጀመረ ሲሆን  ከ 90 በመቶ ስራዉ መጠናቀቅ መቻሉን ሰምተናል።

ከመስከረም ወር አንስቶ የቅርሱ ጥገና ለማስጀመር ጥረቶች ሲደረጉ መቆየታቸውን የገለፁት የትግራይ ቱሪዝም ቢሮ ምክትል ሀላፊ አቶ ሀይላል በየነ በመጪዉ መጋቢት ወር ጥገናዉን እንደሚጠናቀቅለት ገልፀዋል።

በሰሜኑ ጦርነት የቅርሱ ይዞታ  የከባድ መሳሪያ ጥቃት ሰለባ በመሆኑ የቅርሱን ጥገና በጥንቃቄ ለመስራት ተሞክሯል ተብሏል።

የቅርሱ የእድሳት ስራ ምእራፉን ለማጠናቀቅ ጥቂት ቀሪ ስራዎች ብቻ ቀርተዉታል ነዉ የተባለዉ።

አቶ ሀይላይ ቅርሱን ሀይማኖታዊ አዉዱን  እንዳያጣ ለማድረግ የክልሉ የእስልምና ጉዳዩች በቅርበት ሲከታተለዉ ቆይቷል ብለዋል።

የቅርስ እድሳት ስራዉ በወጪ ደረጃ  የቱርክ ልማት ኤጀንሲ የሸፈነ ሲሆን ቅርስ ጥገናዉን የቴክኒክ እና የማማከር ስራዎችን የቱሪዝም ቢሮዉ እንደከወነ ተናግረዋል።

በትግራይ ክልል የሚገኘዉ የአልነጃሺ ታሪካዊና ሀይማኖታዊ መካነ ቅርስ ሶስት አመታት በዘለቀዉ ጦርነት ቅዱስ እቃዎች እንዲሁም በመስጅዱ የተቀመጡ የቅርስ ይዘት ያላቸዉ መገልገያዎች መዘረፋቸዉን ይታወቃል።

@ኢትዮ ኤፍ ኤም

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ምንገድ ላይ

(በእውቀቱ ስዩም) በቀደም ከሆነ ቦታ ተነስቼ ወደ አልሆነ ቦታ ስራመድ...

ብፁዕ ካርዲናል አቡነ ብርሃነ ኢየሱስ በጡረታ ከኃላፊነታቸው ተሰናበቱ

የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያንና የአዲስ አበባ አገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ...

አትሌት ጉዳፍ ጸጋዬ አዲስ መግለጫ አወጣች

ታዋቂዋ አትሌት ጉዳፍ ጸጋዬ ለስፖርት ወዳጆችና ለደጋፊዎቿ ወቅታዊ መረጃ...