አትሌት ጌታነህ የ10 ኪሎ ሜትር ሩጫ ውድድር  አሸናፊ ሆነ

Date:

አትሌት ጌታነህ ሞላ  በቢሾፍቱ ከተማ በተካሄደው የአየር ኃይል 90ኛ ዓመት የምስረታ በዓል የ10 ኪሎ ሜትር ሩጫ አሸናፊ ሆኗል።
የኢፌዴሪ አየር ኃይል 90ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን በተለያዩ ዝግጅቶች እያከበረ ይገኛል።

የምስረታ በዓሉ አካል የሆነው ቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ የ10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ እየተካሄደ ነው።

በጎዳና ላይ ሩጫው ከጎረቤት ሀገራት ጭምር አትሌቶች  ተሳታፊ ሆነዋል።
በሩጫው በሁለቱም ጾታዎች ለሚያሸንፉ ተወዳዳሪዎች በተመሳሳይ 500 ሺህ ብር ሽልማት ይበረከትላቸዋል።

ሁለተኛ ደረጃን  ይዘው ለሚያጠናቅቁ 250 ሺህ ብር፣ ሶስተኛ ደረጃ ለሚወጡ 100 ሺህ ብር፣ አራተኛ ለሚወጡ 50 ሺህ ብር እና አምስተኛ ለሚወጡ አትሌቶች የ25 ሺህ ብር ሽልማት እንደሚበረከትላቸውም ተገልጿል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...