“ከ 11 ሰዓት ተኩል በፊት [ከቢሮ] ለሚወጣ የመንግሥት ሠራተኛ የትራንስፖርት አገልግሎት አይሰጥም”

Date:

ለመንግሥት ሠራተኞች በነፃ የትራንስፖርት አገልግሎት እየሰጡ የሚገኙት የፐብሊክ ሰርቪስ የትራንስፖርት አውቶብሶችን በሥራ መውጫ ሰዓት ከ 11 ሰዓት ተኩል በፊት መጠቀም እንደማይቻል የአዲስ አበባ የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ አስታውቋል።

ቢሮ እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው “የመንግሥት የሥራ ሰዓት ከመድረሱ በፊት” ባሶቹን የሚጠቀሙ ሠራተኞች በመኖራቸው መሆኑን አስታውቋል።

በቢሮ ተጽፎ ለሁሉም ክፍለከተማዎች በተሰራጨው ደብዳቤ ላይ፤  “የመንግሥት ሠራተኞች የሥራ ሰዓትን በአግባቡ ሥራ ላይ እንዲያውሉ መንግሥት የፐብሊክ ትራንስፖርት አገልግሎት በማመቻቸቱ እና አብዛኛው ሠራተኛ ተጠቃሚ በመሆኑ ከእንግልት መትረፉን” ይገልፃል።

ኢትዮቲዩብ የተመለከተው ደብዳቤ የመንግሥት ሠራተኛው ነፃ የትራንስፖርት አገልግሎት ተጠቃሚ መሆኑ “ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ  እንዲያገኝ” ስለማድረጉ ያትታል።

ሆኖም ባሶቹ የሥራ መውጫ ሰዓት ከመድረሱ በፊት ሠራተኛውን እንደሚጭኑ ተነግሯል። ይህ ተግባር “በመንግሥት ሥራ ላይ ከፍተኛ ጫና እያሳደረ እንደሚገኝ ቢሮ አስታውቋል።

በዚህ ሳቢያ የፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አውቶብሶች “በተመደቡበት የመነሻ ቦታ ሠራተኞችን ከሰዓት ከ 11:45 በኋላ መጫን  እንዲጀምሩ” ለሁሉም ክፍለክተማ የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ጽሕፈት ቤት መመሪያ ተላልፏል።

ሁሉም  የፐብሊክ ትራንስፖርት ተጠቃሚ ይህን የሰዓት ለውጥ በመገንዘብ ከ 11 ሰዓት ተኩል በፊት ከመሥሪያ ቤቱ እንዳይወጣ ቢሮ አሳስቧል። በዚህ ረገድ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶችም ሠራተኞቻቸው በአግባቡ እንዲቆጣጠሩ በተጻፈው ደብዳቤ ላይ ተመላክቷል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ደቡብ ሱዳን የነዳጅ ቅድመ-ክፍያ ውሎችን እንዳትፈጽም አገደ

የለንደን ፍርድ ቤት ደቡብ ሱዳን ከአሁን በኋላ አዳዲስ የነዳጅ...

” ከ140 በላይ ጠጠር አምራች ድርጅቶች ሙሉ በሙሉ ቆመዋል ” – ማህበሩ

" ካላቸው ቅሬታ ማቅረብ ይችላሉ። ግን መሬቱ መቼ እንደተወሰደባቸው...

ትራምፕ “በኢራን ላይ ሊፈጸም ታቅዶ የነበረውን ጥቃት አንፈጽምም” አሉ

ትራምፕ በመካከለኛው ምስራቅ የሚገኙ ቁልፍ የአሜሪካ አጋር ሀገራት መሪዎች...

በነዳጅ ጭማሪ በኬንያ በተቀሰቀሰ ተቃውሞ የአራት ሰዎች ሕይወት አለፈ

በኬንያ የነዳጅ ዋጋ ጭማሪን ተከትሎ በዋና ከተማዋ ናይሮቢ በጸጥታ...