ኮሚሽኑ በከፍተኛ ባለስልጣናት ለሚፈጸሙ የሙስና ወንጀሎች ማስረጃ ማግኘት ፈተና እንደሆነበት ገለጸ

Date:

ከፍተኛ የመንግሥት ሹመኞች የሚፈጽሟቸውን እንደ የሕዝብ ሀብት ምዝበራ ያሉ የሙስና ወንጀሎች ለመከላከልና ጥፋተኞችን ተጠያቂ ለማድረግ የሚያስችሉ ጠንካራ ማስረጃዎች ማግኘት ትልቁ ፈተና መሆኑን የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ገልጿል።

አንዳንድ ከፍተኛ ኃላፊዎች የመንግሥትን ፖሊሲና አሠራር በማዛባት የሕግ የበላይነትን እና የኢኮኖሚ መረጋጋትን ለመፍጠር የሚደረጉ ጥረቶችን እያሰናከሉ መሆኑን የሕግ ባለሙያዎች በተደጋጋሚ ቢያነሱም፤ የተጠረጠሩትን ባለስልጣናት ፍርድ ቤት ለማቅረብ የሚያስችል ማስረጃ ማግኘት ግን አስቸጋሪ ነው ተብሏል።

በኮሚሽኑ የሙስና መረጃዎች አስተዳደር መሪ ሥራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን በላይነህ፤ “በተቋማት አመራሮች አማካኝነት የሚፈጸሙ ወንጀሎችን ለመከላከልና ጥፋት ፈጻሚዎችን ለማስቀጣት ከወሬ የዘለለ የሰው እና የሰነድ ማስረጃዎችን ማግኘት አስቸጋሪ ነው፤ ተጨባጭ ማስረጃ ሳይገኝ ደግሞ አንድን ግለሰብ የሕግ ተጠያቂ ማድረግ አይቻልም” ሲሉ ለአሐዱ ሬዲዮ ተናግረዋል።

“ሙስና በፈጻሚዎቹ ስልጣን እና ኃላፊነት እንዲሁም በዓይነቱ በ4 ደረጃዎች አሉት” በማለት ያብራሩት አቶ መስፍን፤ በከፍተኛ ሹማምንት የሚፈጸመውን መጠነ ሰፊ፣ በታችኛው መዋቅር ሹመኞች የሚፈጸመውን ጥቃቅን፣ በፖለቲካዊ ውሳኔ የሚፈጸመውን የፖለቲካ፣ ሕጋዊ መንገድን በተከተለ የሕግ ክፍተት የሚፈጸመውን ስርአታዊ በማለት ከፋፍለው አቅርበውታል።

ሥራ አስፈጻሚው በመጨረሻም፤ “እስካሁን ለፈጸመው የሕዝብ እና መንግሥት ንብረት ምዝበራ ሙስና ወንጀል ማስረጃ ተገኝቶበት በሕግ ተጠያቂ ያልሆነ የመንግሥት ኃላፊ የለም” ብለዋል።

(አሐዱ ሬዲዮ)

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ደቡብ ሱዳን የነዳጅ ቅድመ-ክፍያ ውሎችን እንዳትፈጽም አገደ

የለንደን ፍርድ ቤት ደቡብ ሱዳን ከአሁን በኋላ አዳዲስ የነዳጅ...

” ከ140 በላይ ጠጠር አምራች ድርጅቶች ሙሉ በሙሉ ቆመዋል ” – ማህበሩ

" ካላቸው ቅሬታ ማቅረብ ይችላሉ። ግን መሬቱ መቼ እንደተወሰደባቸው...

ትራምፕ “በኢራን ላይ ሊፈጸም ታቅዶ የነበረውን ጥቃት አንፈጽምም” አሉ

ትራምፕ በመካከለኛው ምስራቅ የሚገኙ ቁልፍ የአሜሪካ አጋር ሀገራት መሪዎች...

በነዳጅ ጭማሪ በኬንያ በተቀሰቀሰ ተቃውሞ የአራት ሰዎች ሕይወት አለፈ

በኬንያ የነዳጅ ዋጋ ጭማሪን ተከትሎ በዋና ከተማዋ ናይሮቢ በጸጥታ...