የተመድ አዲስ ማስጠንቀቂያ ለእስራኤል

Date:

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እስራኤል በደቡብ ሊባኖስ ሰላም አስከባሪ ሃይል አቅራቢያ የምትፈጽመውን ጥቃት እንድታቆም አስጠነቀቀ።

የእስራኤል ጦር  በደቡባዊ ሊባኖስ በሚገኘው የተባበሩት መንግስታት ሰላም አስከባሪ ሃይል አቅራቢያ እየፈጸመ ያለውን ተከታታይ የአየር ጥቃትን ሊያቆም ይገባል ሲል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) ለእስራኤል አዲስ ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል።

ጥቃቱ የፀጥታው ምክር ቤት ውሳኔን በግልጽ የጣሰ ነው ሲልም ድርጅቱ አውግዟል።

የተመድ ጸጥታው ምክር ቤት ቃል አቀባይ ስቴፈን ዱጃሪክ፥ በደቡባዊ ሊባኖስ ተሰማርቶ የሚገኘው የተባበሩት መንግስታት ሰላም አስከባሪ ሃይል (UNIFIL) በሚንቀሳቀስበት አካባቢ ተከታታይ የአየር ድብደባዎችን መመልከቱን ተናግረዋል።

ቃል አቀባይ በሰላም አስከባሪ ሃይሎች ላይ የሚሰነዘረው ጥቃት ተቀባይነት የሌለው እና የጸጥታው ምክር ቤትን ውሳኔ ቁጥር 1701 የጣሰ ከባድ ጥሰት ነው ብለዋል።

የሊባኖስ ባለስልጣናት የሰላም አስከባሪዎችን ደህንነት እንዲያረጋግጡ እና ወንጀለኞችን ለፍርድ ለማቅረብ ድርጊቱን በአስቸኳይ ሊመረምሩ ይገባል ሲሉም ጠይቀዋል።

በተጨማሪም የእስራኤል ጦር የደህንነት ችግሮችን ለመፍታት ያለውን የግንኙነት እና የማስተባበር ዘዴዎችን እንዲጠቀም ሲሉም ነው ቃል አቀባዩ ያሳሰቡት።

ባለፈው አመት በእስራኤል እና በሊባኖስ መካከል የተኩስ አቁም ስምምነት ቢደረግም፥ ሁከትን ሙሉ በሙሉ ማስቆም ሳይቻል ዛሬም አለመረጋጋቶች ይስተዋላሉ።

የተኩስ አቁም ስምምነቱ በህዳር 2024 ተግባራዊ ከሆነ በኋላ፥ የሊባኖስ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ከ1ሺ በላይ በሆኑ የእስራኤል ጥቃቶች ቢያንስ 335 ሰዎች መሞታቸውን እና 973 መቁሰላቸው መረጋገጡን አሳውቋል።

የእስራኤል ጦር በጥር 2025 ከደቡብ ሊባኖስ ሙሉ በሙሉ ለቆ እንዲወጣ ድረስም የተደረሰውን የተኩስ አቁም ውል በመጣስ በአምስት የድንበር ማዕከሎች ወታደሮቹን ማስገባቱን ጠቅሶ የዘገበው ሚድል ኢስት ሞኒተር ነው።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...