የኢትዮጵያ አየር መንገድ ባወጣው መግለጫ በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች ጭጋጋማ እና ለበረራ አመቺ ያልሆነ የአየር ፀባይ አጋጥሞኛል ብሏል።
የተሰበሰበ የሚቲዎሮሎጂ መረጃ ይህ የአየር ፀባይ ለተወሰኑ ቀናት የሚቀጥል መሆኑን አረጋግጧል ብሏል መግለጫው።
በዚህ ምክንያት ወደተወሰኑ የሀገሪቱ ክፍሎች የሚደረጉ በረራዎችን ለማቋረጥ በመገደዱን ተናግሯል።
የአየር ፀባዩ እስከሚስተካከል እና በረራዎችን መቀጠል እስከሚቻል ድረስ መንገደኞች እንዲታገሱ ጠይቋል።
አስቸኳይ ጉዞ ያለባቸው መንገደኞችም ሌላ የጉዞ አማራጭ ይጠቀሙ ብሏል።
አየር መንገዱ በአየር ፀባይ ምክንያት የተስተጓጎሉ በረራዎች ወደ መደበኛ አገልግሎታቸው እንደተመለሱ ለመንገደኞች አሳውቃለው ብሏል በመግለጫው።
በዚህ ምክንያት ለሚፈጠሩ መጉላላቶችም ይቅርታ ጠይቋል።
