ፕሬዝደንት ትራምፕ የሩሲያ ነዳጅ ገዢዎችን ኢላማ ያደረገ ረቂቅ ሕግ ማጽደቃቸውን ተከትሎ፤ ቤጂንግ ከሞስኮ ጋር ያላትን የንግድ ግንኙነት በአስቸኳይ እንድታቆም ማስጠንቀቂያ ሰጥተዋል።
ቻይና ከሩሲያ ጋር ያላትን የንግድ ግንኙነት እንድታቆም አሜሪካ ብትጠየቅም፤ቤጅንግ በሰጠችው ምላሽ ከሩሲያ ጋር ያላትን የኢኮኖሚ እና የንግድ ግንኙነት ለማበላሸት የሚደረግ ማንኛውንም ሙከራ እንደማትቀበል አስታውቃለች።
ቤጂንግ ሁልጊዜም ሕገ-ወጥ እና የአንድ ወገን ማዕቀቦችን ትቃወማለች ሲሉ የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማኦ ኒንግ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።
ቻይና ከሩሲያ ጋር ያላት መደበኛ የኢኮኖሚ እና የንግድ ግንኙነት ህጋዊነት ያለው ነው ሲሉም አክለዋል።
ሆኖም በዶናልድ ትራምፕ ይሁንታ የፀደቀው ረቂቅ ሕግ እንደ ቻይና፣ ህንድ እና ብራዚል ባሉ አገሮች ላይ ማዕቀብ በመጣል ሩሲያ በዩክሬን ላይ እያካሄደችው ባለው ጦርነት የሚደርሳትን ድጋፍ ለማዳከም ያለመ ነው ሲል የዘገበው አርቲ ኒውስ ነው።
