ኢትዮጵያ ከዓለም ሁለተኛ ሆና አጠናቀቀች

Date:

በአሜሪካ ፍሎሪዳ በድምቀት የተከናወነው 46ኛው የአለም አገር አቋራጭ ውድድር ፍፃሜውን አግኝቷል ።

የ2026 አለም አገር አቋራጭ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ ከዓለም ሁለተኛ ደረጃን ይዛ አጠናቀቀች።

ፈታኝ እና ከፍተኛ ፉክክር በተደረገበት ውድድር ኢትዮጵያ በመድረኩ ባስመዘገቻቸው አጠቃላይ ሰባት ሜዳሊያዎች ኬኒያን ተከትላ ከዓለም ሁለተኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች።

485 አትሌቶች ከተለያዩ 52 የአለም ሀገራት በተፎካከሩበት  ውድድር ምንም እንኳን በወጣት ወንድ አንድ አትሌት ብቻ እና በሴቶች ወጣት 3 አትሌቶች ብቻ በቪዛ ምክንያት ማሰለፍ ባለመቻላችን የቡድን ውጤት ሊመዘገብልን ባይችልም በተሰለፋት ልጆቻችን ኢትዮጵያ በሶስት የወርቅ፣በሁለት የብር እና በሁለት የነሃስ  ሜዳሊያዎች ነው በኬኒያ ብቻ ተበልጣ ሁለተኛ ሆና አጠናቃለች።

ኢትዮጵያ በአዋቂ ወንዶች እና ሴቶች 10 ኪ.ሜ በቡድን ሁለት የወርቅ ሜዳሊያ በማስመዝገብ በመድረኩ ታሪክ ስትሰራ ፣ በአትሌት ማርታ አለማየው ወርቅ ፣በአዋቂ ወንዶች በአትሌት ሪሁ አረጋዊ እና በወጣት ሴቶች አትሌት ወሰኔ አሰፋ የብር ሜዳሊያ እና በድብልቅ ሪሌይ በቡድን የነሃስ በአዋቂ  ሴቶች በአትሌት ሰናይት ጌታቸው የነሃስ ሜዳሊያዎችን አሸንፋለች።

በመድረኩ ኢትዮጵያን ወክላችሁ ድል ላስመዘገባችሁ ብርቅዬ አትሌቶቻችን እንኳን ደስ አላችሁ ። እንኳን ደስ አላችሁ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለ10 ምሁራን የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ሰጥቷል

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር ቦርድ ጥቅምት 12 ቀን 2019...

ዳሸን ባንክ እና ሼባ ማይልስ የፕላቲንየም ብራንድ የማስተር ካርድ ይፋ አደረጉ

ዳሸን ባንክ እና ሼባ ማይልስ በኢትዮጵያ ለሚገኙ ደንበኞች የፕሪሚየም...

የአሜሪካ የደህንነት ኃላፊ ኢራንን አስጠነቀቁ

ቡሔራዊ ደህንነት ዳይሬክተር ጄይ ክላይተን አርብ ዕለት ኢራን በውጭ...

ኢትዮጵያ በግብርናው ዘርፍ  በአመት ከ1.1 ቢሊዮን ዶላር በላይ ታጣለች

85 በመቶ የሚሆነው የኢትዮጵያ ህዝብ በግብርናው ዘርፍ የተሰማራ ሲሆን...