ዋና ጸሐፊው አንቶኒዮ ጉተሬዝ፣ ዛሬ በይፋ በጀመረው 39ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ ላይ ባደረጉት የመክፈቻ ላይ ንግግር “ያለነው 2026 ላይ እንጂ 1946 አይደለም” ብለዋል፡፡
የአፍሪካ የምክር ቤቱ አባል አለመሆን “ምንም አይነት አመክንዮ ሊቀርብለት የማይችል” ጉዳይ እንደሆነም ገልጸዋል ።
ዋና ጸሐፊው አክለውም ወደፊት ምንም ዓይነት ማሻሻያዎች ወይም ውሳኔዎች ቢተላለፉ፣ አፍሪካ በዓለም አቀፍ የውሳኔ ሰጪነት ጠረጴዛ ላይ ቋሚ ቦታ ሊኖራት እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡
የካቲት 07/2018 ዓ.ም
