የምክር ቤቱ አባላት ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ካቀረቧቸው ጥያቄዎች እና አስተያየቶች መካከል:-

Date:

👉የኢትዮጵያን የባህር በር ጥያቄ ለመመለስ መንግስት እያካሄደ የሚገኘው የዲፕሎማሲ ስራ እጅግ የሚበረታታ ነው፥

👉በኢትዮጵያ ከከተማ እስከ ገጠር እየተካሄደ የሚገኘው የኮሪደር ልማት የኢትዮጵያን ገጽታ የሚቀይር ነው፥

👉በትግራይ ክልል የሚታየው የፖለቲካ ልዩነት በሰላም እንዲፈታ ምን እየተሰራ ነው? የፕሪቶሪያው ስምምነት ለምን አልተተገበረም?

👉በሀገሪቱ ታላላቅ ፕሮጀክቶችን ጀምሮ የማጠናቀቅ እና አዳዲስ ፕሮጀክቶችን የመጀመር ስራ ተጠናክሮ ቀጥሏል፤ይህ ኢትዮጵያ ያለችበትን ለውጥ ያመለክታል፥

👉በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ዜጎች በሽፍቶች፤በጽንፈኞች ይገደላሉ፤ይታገታሉ፤ይዘረፋሉና መፍትሄ ቢሰጥ፣

👉መንግስት ጨካ ገብተው ህዝብን ለችግር ከሚዳርጉ ሃይሎች ጋር ልዩነቶችን በሰላም ለመፍታት ምን እየሰራ ይገኛል?

👉መንግስት በነዳጅ ላይ ድጎማ ቢያደርግም በአንዳንድ ክልሎች የነዳጅ ዋጋው በከፍተኛ ደረጃ ጨምሯል።ይህም በህገወጦች እጅ በመግባቱ እንደሆነ ህብረተሰቡ ቅሬታውን ያነሳል። ቁጥጥሩን ለማጠናከር መንግስት ምን እየሰራ ነው?

👉 በሀገሪቱ የዋጋ ንረት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የሸማቹን የመግዛት አቅም እየተፈታተነ ይገኛል

👉መንግስት ለግብርናው ዘርፍ የሰጠው ከፍተኛ ትኩረት ተጨባጭ በሆነ መልኩ ምርታማነትን አሳድጓል የሚሉት ይገኙበታል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የኢራን ተፈጥሮአዊ ምሽጎች እና ስትራቴጂካዊ ጥበብ

​ግዮን መጽሔት :- በመካከለኛው ምስራቅ የጂኦ-ፖለቲካ ትኩሳት...

ለአድዋ ድል መታሰቢያ በአሜሪካ ቀን ተሰየመ

በአሜሪካ፣ የፔንሲልቪኒያ ግዛት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የአውሮፓዊያኑ 'መጋቢት...

ኢሎን መስክ የዓለማችን የመጀመሪያው ትሪሊዮነር ሆነ

ኢሎን መስክ የሀብት መጠኑ 1 ትሪሊዮን ዶላር ያለፈ የመጀመሪያው...

የእግር ኳስ ዳኝነት በኢትዮጵያ

ገነነ መኩሪያ (ሊብሮ) ግዮን መጽሔት :- እግር ኳስ...