ትራምፕ ጋዛን ሊገነቡ ይሆን?

Date:

በጋዛ ለሚሰማራው የሰላም አስከባሪ ሀይል ሀገራት ወታደሮቻቸውን ለመላክ  መዘጋጀታቸውን አስታወቁ።

ኢንዶኔዥያ ፣ ሞሮኮ፣ ካዛኪስታን ፣ ኮሶቮ እና አልባኒያ ወታደሮቻቸውን እንደሚልኩ ገልፀዋል።

የአሜሪካ ከፍተኛ  ወታደራዊ አዛዥ ጀኔራል ጃስፐር ጀፈርስ በዋሽንግተን የመጀመሪያውን የሰላም ቦርድ ስብሰባ አድርገዋል።

ወታደሮቹ ዓለም አቀፍ የሰላም አገልግሎት ሰጭ በመሆን የሚያገለግሉ ሲሆን፣ ግብፅ እና ዮርዳኖስ የፍልስጤምን ፖሊስ ያሰለጥናሉ ተብሏል።

ጀኔራል ጃስፐር ወታደሮቹ በመጀመሪያው ዙር በራፋህ እንዲሰፍሩ ይደረጋል፣ ቀስ በቀስ ወደሌሎች ስፍራዎች እንደሚሰማሩ ተናግረዋል።

12 ሺህ  ፖሊሶችና  20 ሺህ ዓለም አቀፍ ድጋፍ ሰጭ ወታደሮች እንደሚሰማሩም አክለው ገልፀዋል ጄነራል ጃስፐር።

በፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የተቋቋመው የሰላም ቦርድ ኮሜቴ እንደገለፀው፣ በራፋህ 100 ሺህ ቤቶች፣500 ሺህ መኖሪያዎችእና 400 ሺህ ተጨማሪ  ቤቶች በጋዛ  ይገነባሉ ሲል አስታውቋል ።

በዚህ የሰላም ቦርድ እስካሁን ድረስ  26 ሀገራት በአባልነት  ተመዝግበዋል።  ሀማስ ግን በጉዳዩ ዙሪያ  እስከዚህ ሰዓት ድረስ የሰጠው መግለጫ የለም። አርቲ ኒውስ እንዳስነበበው ።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የተፈናቀሉ ዜጎች በተጠለሉበት አካባቢ በቋሚነት መኖር የሚያስችላቸው 

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን የዳሰነች ወረዳ ከበኦሞ...

ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ 11ኛውን የኃይሌ ሆቴልና ሪዞርት በደብረ ብርሃን ከተማ አስመረቀ

ታዋቂው አትሌትና ባለሀብት ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ፣ በደብረ ብርሃን ከተማ...

በኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር የተዘጋጀው የመጀመሪያው አህጉራዊ የሪል ስቴት ኤግዘቢሽን ተከፈተ

በኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር አዘጋጅነት የመጀመሪያው አህጉራዊ የሪል...

በሊባኖስ እና በእሰራኤል የተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት ተራዘመ

ትራምፕ በሊባኖስ እና በእሰራኤል መካከል የተደረሰው የተኩስ አቁም በሦስት...