ኢትዮጵያ የመጀመሪያዎቹን የኢንቨስትመንት ባንኮች እና የሰነድ ሙዓለንዋይ ገበያ አከናዋኝ አገኘች

Date:

የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለሥልጣን ለአምስት አዳዲስ ድርጅቶች የካፒታል ገበያ አገልግሎት ሰጪ ፈቃድ መስጠቱን አስታውቋል።

ይህ ውሳኔ በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የኢንቨስትመንት ባንኮችና የሰነድ ሙዓለንዋይ ገበያ አከናዋኝ ፈቃድ የተሰጠበት እንዲሁም አጠቃላይ ፈቃድ የተሰጣቸው የካፒታል ገበያ አገልግሎት ሰጪዎች ቁጥር ከአራት ወደ ዘጠኝ ከፍ ያደረገበት ነው።

ፈቃድ የተሰጣቸው ድርጅቶች ሲቢኢ ካፒታል አ.ማ – ኢንቨስትመንት ባንክ ፣ ወጋገን ካፒታል ኢንቨስትመንት ባንክ አ.ማ – ኢንቨስትመንት ባንክ ፣ ኢትዮ-ፊደሊቲ ሴኩሪቲስ አ.ማ – የሰነድ ሙዓለንዋይ ገበያ አከናዋኝ (Securities Dealer) ፣ ኤች ኤስ ቲ ኢንቨስትመንት አድቫይዘሪ ሰርቪስስ ኃ.የተ.የግ. ማ – የሰነድ ሙዓለንዋይ ኢንቨስትመንት አማካሪ ፣ ኢኩዥን የሰነድ ሙዓለንዋይ ኢንቨስትመንት አማካሪ ኃ.የተ.የግ. ማ – የሰነድ ሙዓለንዋይ ኢንቨስትመንት አማካሪ መሆናቸው ተጠቁሟል ።

ይህ ታሪካዊ ክስተት የኢትዮጵያን የፋይናንስ ገበያ ለማሳደግና ለኢንቨስትመንት እድሎች መስፋፋት ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ተገልጿል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ግዮን መጽሔት በዛሬ ዕትሟ

ግዮን መጽሔት ዛሬ ቅዳሜ ነሔሴ 16 2018 ዓ.ም ገበያ...

ቱርክ ቤንያሚን ኔታንያሁ ላይ የእስር ማዘዣ አወጣች

ቱርክ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ላይ ዓለም አቀፍ...

በመቀለ የሚካሄደው የአሸንዳ በዓል የመክፈቻ ሥነ ሥርዓት ተሰረዘ

በትግራይ በርካታ ታዳሚ በሚገኝበት በየዓመቱ የሚከበረው የአሸንዳ ባህላዊ በዓል...

የኢትዮጵያ ፖስታ 3 ሺሕ የሚጠጉ ቅርንጫፎቹን ወደ ባንክ ኤጀንትነት ለመቀየር እንቅስቃሴ ጀመረ

የኢትዮጵያ ፖስታ በመላ ሀገሪቱ የሚገኙ 3 ሺሕ በሚጠጉ ቅርንጫፎቹ...