በኢትዮጵያ የከብቶች ሳንባ በሽታን ለመዋጋት ምርመራ እና ልየታ

Date:

በጣም ተላላፊ እና አደገኛ የሆነው የባክቴሪያ በሽታ ከብቶችን እና ሌሎች የቤት እንስሳትን ያጠቃል። በኢትዮጵያ ብቻ በግምት 3.8 ሚሊዮን ከብቶችን እንደሚያጠቃ ጥናቶች የሚጠቁሙ ሲሆን በዚህም ሀገሪቱ 2.4 በመቶ ከእንስሳት ወደ ሰው ለሚተላለፍ የሳንባ በሽታ ተጋላጭ ናት።

በሽታውን ለመቆጣጠር የተለመደው አሠራር መርምሮ በበሽታው የተያዙትን ማረድ ቢሆንም ኢትዮጵያ እና ሌሎችም ሀገራት በኢኮኖሚ፣ መሠረተ ልማት፣ ሐይማኖታዊ እና ባሕላዊ ምክንያቶች ይህን ዘዴ አይጠቀሙም።

የበሽታውን ስርጭት ለመከላከል ከብቶችን መርምሮ ባክቴርያው የተገኘባቸውን በመለየት ቀሪዎቹን የመከላከል ዘዴ ውጤታማ እንደሆነ በሰበታ የእንስሳት ጤና ኢንስቲትዩት የእንስሳት ሐኪምና ተመራማሪ ዶ/ር ማቲዮስ ላቀው ገልፀዋል።

መርምሮ በበሽታው የተያዙትን የማረድ ዘዴ ብዙ መሠረተ ልማት ባይጠይቅም መርምሮ ከመለየት በሁለት እጥፍ ወድ እንደሆነ ጥናቱ ማረጋገጡን ባለሙያው ጨምረው ገልፀዋል። ሆኖም እርሻዎች በቲቢ የተያዙትን ካልተያዙት የሚለይ በቂ የለይቶ ማቆያ ቦታ ሊኖራቸው እንደሚገባ ጠቁመዋል።

የዓለም ቲቢ ቀን በየዓመቱ መጋቢት 15 ቀን የሚከበር ሲሆን ቀኑ ቲቢን መከላከልና መቆጣጠር አስፈላጊ እንደሆነ በማጉላት ታስቦ ይውላል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...