ይህ የምዝገባ ሂደት በቀጣይ መጋቢት 15 ቀን 2018 ዓ.ም እንደሚጠናቀቅ የትምህርት ምዘና ፈተናዎች አገልግሎት ኤጀንሲ አስታውቋል ።
የኤጀንሲው የፈተና አስተዳደር ስራ አስፈፃሚ አቶ ወንደሰን የሱስወርቅ በሀገር አቀፍ ደረጃ የ12ኛ ክፍል ፈተናን ለመፈተን የተመዘገቡ ተማሪዎች ቁጥር ከፍተኛ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚሰጠውን የ12ኛ ክፍል ፈተናን ለመፈተን ቀድመው የተመዘገቡት የትግራይ ክልል ተማሪዎች እንደሆኑ የተናገሩት ስራ አስፈፃሚው ምዝገባው የተጀመረው ከየካቲት 18 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ እንደሆነ ጠቁመዋል ።
ምዝገባውን ለማከናወን በአንዳንድ አከባቢዎች የኔትወርክ መጨናነቅ ፣ የኤሌትሪክ ሀይል አለመኖር እንዲሁም ደግሞ የፍይዳ መታወቂያ ያላወጡ ተማሪዎቹ መኖራቸውን እንደ ችግር አንስተዋል ።
እስከ አሁን የ12 ኛ ክፍል ተማሪዎች ምን ያህ ተመዝግበዋል የሚለው ከአሐዱ ለቀረበላቸው ጥያቄ በአሁኑ ወቅት ምን ያህል እንደሆነ ለመናገር እንደተቆጡቡና ነገር ግን መጋቢት 15 ቀን 2018 ዓ.ም ኤጀንሲው ይፍ እንደሚያደርግ ተናግረዋል ።
በትግራይ ክልል የሚገኙ 100 የሚሆኑ ተማሪዎች ከፋይዳ መታወቂያ ጋር በተያያዘ ያልተመዘገቡ ተማሪዎች ይኑሩ እንጂ እስከ አሁን ባለው ሁኔታ ከሌሎች ክልሎች በተሻለ ሁኔታ እያስመዘገበ መሆኑን ተናግረዋል ።
በተመሳሳይ የግል ተፈታኝ የሆኑ ተማሪዎች 30 በመቶ የተመዘገቡ ሲሆን ተፈታኞቹም እስከ መጋቢት 30 ቀን 2018ዓ.ም የሚጠናቀቅ መሆኑን አስረድተዋል ።
የትግራይ ክልል ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶክተር ኪሮስ ጎሹን አሐዱ ያናገረ ሲሆን በክልሉ የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተናን የሚወስዱ 30 ሺህ ተማሪዎች መመዝገባቸውን ተናግረዋል፡፡
በዚህም መሰረት 90 በመቶ የሚሆኑ ተማሪዎች መመዝገባቸውን ጠቅሰው በአሁኑ ወቅት ለክልሉ ከ2018 ዓ.ም ጥቅምት ወር ጀምሮ ከፌዴራል መንግስት በጀት እንዳልተለቀቀለት ተናግረዋል ።
በተለይ ለምዝገባው ቅድሚያ በመስጠት ለመምህራን ስልጠና እንዲሰጥ ከተደረገ በኋላ የኦንላይን ምዝገባ ተማሪዎቹ እንዲመዘገቡ ተደርጓል ብለዋል። ነገር ግን ተማሪዎቹ ተመዘገቡ ማለት ግን ለፈተና እየተዘጋጁ ነው ማለት እንደማይቻል ገልፀዋል በአሁኑ ወቅት በክልሉ ትምህርት ሊዘጋ እንደሚችል ጠቁመዋል።
