ኢትዮጵያ እና ጀርመን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የጀመሩበትን 120ኛ ዓመት ያከብራሉ

Date:

በጀርመን የኢትዮጵያ አምባሳደር እስክንድር ይርጋ ከጀርመን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከሰሃራ በታች አገራት እና ሳሄል ዳይሬክተር አምባሳደር ክርስቶፍ ሬትዝላፍ ጋር ዛሬ ውይይት አድርገዋል።

ውይይቱ የሁለቱን ሀገራት የሁለትዮሽ ግንኙነት ማጠናከርን ያለመ ነው።

ሀገራቱ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙታቸውን የጀመሩበት 120ኛ ዓመት በጋራ በሚያከብሩበት ሁኔታ ላይ መምከራቸውንም በበርሊን የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመለክታል።

ኢትዮጵያ እና ጀርመን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን የጀመሩት እ.አ.አ በ1905 መሆኑን መረጃዎች ያመለክታሉ።

ሁለቱ ሀገራት በየሀገራቱ ኤምባሲያቸውን የከፈቱት እ.አ.አ በ1907 ነው።

ግብርና፣ ምግብ ዋስትና፣ ትምህርት፣ ማህበራዊ ዋስትና እና የግሉ ዘርፍ አቅም ግንባታ ከኢትዮ-ጀርመን የትብብር መስኮቹ መካከል ይጠቀሳሉ።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ግዮን መጽሔት በዛሬ ዕትሟ

ግዮን መጽሔት ዛሬ ቅዳሜ ነሔሴ 16 2018 ዓ.ም ገበያ...

ቱርክ ቤንያሚን ኔታንያሁ ላይ የእስር ማዘዣ አወጣች

ቱርክ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ላይ ዓለም አቀፍ...

በመቀለ የሚካሄደው የአሸንዳ በዓል የመክፈቻ ሥነ ሥርዓት ተሰረዘ

በትግራይ በርካታ ታዳሚ በሚገኝበት በየዓመቱ የሚከበረው የአሸንዳ ባህላዊ በዓል...

የኢትዮጵያ ፖስታ 3 ሺሕ የሚጠጉ ቅርንጫፎቹን ወደ ባንክ ኤጀንትነት ለመቀየር እንቅስቃሴ ጀመረ

የኢትዮጵያ ፖስታ በመላ ሀገሪቱ የሚገኙ 3 ሺሕ በሚጠጉ ቅርንጫፎቹ...