በኢራን ምድር በሚደረግ ማንኛውም የአሜሪካ የምድር ውጊያ የእስራኤል ጦር አይሳተፍም

Date:

አሜሪካ በኢራን ላይ የምድር ወረራ ለማካሄድ እያመነታች ባለችበት በዚህ ወቅት፣ እስራኤል በየትኛውም የአሜሪካ የምድር ዘመቻ ላይ ወታደሮቿን እንደማታሰማራ አስታወቀች።

የእስራኤሉ ቻናል 12 እንደዘገበው፣ ዋሽንግተን የምድር ጥቃት ለመሰንዘር ከወሰነች እስራኤል ጉዳዩን ለአሜሪካ ጦር ብቻ እንደምትተወውና “የእስራኤል ወታደሮች በምድር ውጊያው ላይ እንደማይሳተፉ” አመልክቷል።

ይህ ዘገባ የወጣው የፔንታጎን ወታደራዊ እቅድ አውጪዎች እንደ ድንገተኛ ወረራ (limited raids) ያሉ አማራጮችን እያዘጋጁ መሆናቸው በተሰማበት ወቅት ነው። ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ይህንን እርምጃ ስለማፅደቃቸው ዋይት ሃውስ በይፋ ያረጋገጠው ነገር ባይኖርም፣ የጦር እቅዱ ግን ከፍተኛ ክትትል እየተደረገበት ይገኛል።

ኢራን በበኩሏ ለማንኛውም የአሜሪካ የምድር ጥቃት “አሰቃቂ አጸፋ” እንደምትመልስ አስጠንቅቃለች። የቴህራን ባለሥልጣናት “የአሜሪካ ጦር እግሩን የኢራን መሬት ላይ ከረገጠ እናቃጥለዋለን” ሲሉ ዝተዋል። ወታደራዊ ተንታኞች እንዲህ ዓይነቱ ወረራ እንደ ቬትናም ጦርነት ሁሉ ትልቅ ስትራቴጂካዊ ስህተት ሊሆን እንደሚችል በማስጠንቀቅ ላይ ናቸው።

የእስራኤል ወታደሮቿን አለማሳተፍ መወሰን በአሜሪካ ውስጥ በ “መጀመሪያ አሜሪካ” (America First) ደጋፊዎች እና ፀረ-ጦርነት አቀንቃኞች ዘንድ ከፍተኛ ተቃውሞ ቀስቅሷል።

ተቺዎቹ “ለእስራኤል ጥቅም ተብሎ በሚታሰብ ጦርነት የአሜሪካ ወታደሮች ብቻ መስዋዕት ሊሆኑ አይገባም” በማለት ቅሬታቸውን እየገለጹ ይገኛሉ። በአሁኑ ወቅት ሁኔታው እጅግ አሳሳቢ ደረጃ ላይ የደረሰ ሲሆን፣ የሚቀጥሉት 10 ቀናት የጦርነቱን አቅጣጫ እንደሚወስኑ ተነግሯል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...