በከተማችን አዲስ አበባ ትልቅ የሙዚቃ ኮንሰርት ሊደረግ ነው

Date:

ሽር -ጉድ ኮንሰርት የሚል ርዕስ የተሰጠው አንጋፋ እና ወጣት ድምፃዊያንን አጣምሯል፡፡ ይህ ኮንሰርት ሽር -ጉድ ኢንተርቴመንት አዘጋጅነት በአዲስ አበባ በሚልየም አዳራሽ ለማከናወን ዝግጅቱን ጨርሷል፡፡

በብዙዎች ዘንድ ተወዳጅነትን ያተረፉ በጥምረት በዘመን ትውስታ ውስጥ የማይጠፉ የዘጠናዎቹ አድማቂዎች ከረዥም አመታት በኃላ በመድረክ ዳግም ይገናኛሉ፡፡ ድምፃዊ ጎሳዬ ተስፋዬ እና አለማየሁ ሂርጶ(ኢቫንጋዲ) በተጨማሪ አንጋፋው ድምፃዊ ኤፍሬም ታምሩ ተካቶበታል፡፡በዚህ ትውልድ በብዙ ዘንድ ተወዳጅነት ያተረፈችሁ ድምፃዊ ሜላት ቀለም ወርቅ ትገኝበታለች ተብሏል፡፡

ሽርጉድ ኮንሰርት ቅዳሜ ሚያዝያ 18/2017 በሚልየም አዳራሽ ይገናወናል፡፡ አዘጋጅ ሸርጉድ ኢንተርቴመንት፡፡ ቀኑ ሲደርስ እየተከታተልን የምንገልፅላችሁ ይሆናል

ተመስገን ኡካሬ የሐጌ ልጅ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ግዮን መጽሔት በዛሬ ዕትሟ

ግዮን መጽሔት ዛሬ ቅዳሜ ነሔሴ 16 2018 ዓ.ም ገበያ...

ቱርክ ቤንያሚን ኔታንያሁ ላይ የእስር ማዘዣ አወጣች

ቱርክ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ላይ ዓለም አቀፍ...

በመቀለ የሚካሄደው የአሸንዳ በዓል የመክፈቻ ሥነ ሥርዓት ተሰረዘ

በትግራይ በርካታ ታዳሚ በሚገኝበት በየዓመቱ የሚከበረው የአሸንዳ ባህላዊ በዓል...

የኢትዮጵያ ፖስታ 3 ሺሕ የሚጠጉ ቅርንጫፎቹን ወደ ባንክ ኤጀንትነት ለመቀየር እንቅስቃሴ ጀመረ

የኢትዮጵያ ፖስታ በመላ ሀገሪቱ የሚገኙ 3 ሺሕ በሚጠጉ ቅርንጫፎቹ...