በኢትዮጵያ የከባድ የአዕምሮ ህመም 0 ነጥብ 6 በመቶ እንደሚደርስ ተገለጸ

Date:

በኢትዮጵያ በአሁን ሰአት የከባድ የአዕምሮ ህመም 0 ነጥብ 6 በመቶ እንደሚደርስና ይህም ማለት ከ1 ሺህ ሰው ውስጥ ወደ 5 የሚደርሱ ሰዎች ላይ እንደሚከሰት ተገለጿል::

ይህ የተገለፀው ኤካ ኮተቤ ሆስፒታል በዛሬው እለት ከሚዲያ ባለሙያዎች ጋር ባካሄደው ውይይት ላይ ነው::

በውይይቱ ላይ በ ኤካ ኮተቤ ሆስፒታል የአዕምሮ ህክምና ክፍል ኃላፊ የሆኑት ዶ/ር እስጢፋኖስ እንዳለማው እንደገለጹት የአዕምሮ ህመምን ለማከም የተለያየ የህክምና አማራጭ ያለ ሲሆን በተለያየ የህክምና መንገድ እንዲድን ማድረግ ይቻላል:

ዶ/ር እስጢፋኖስ አክለውም በኢትዮጵያ የድብርት ህመሞች 9 በመቶ እንደሚደርሱ ገልጸዋል::

ኤካ ኮተቤ ሆስፒታል በአሁን ሰዓት የአዕምሮ ህመም ህክምናን ከሌሎች ህክምናዎች ጋር በማቀናጀት እየሰራ እንደሚገኝና 145 የሚደርሱ የአዕምሮ ህመም ታካሚን አስተኝቶ ለማሳከም የሚያስችሉ አልጋዎች እንዳሉት ተጠቁሟል::

ሆስፒታሉ የሚሰጠውን የህክምና አገልግሎት በተሻለ መልኩ ለማከናወን የእድሳትና የማስፋፊያ ስራ እያካሄደ እንደሚገኝ ተገልጾ እድሳቱ እየተከናወነ የሚገኘው በጤና ሚኒስቴር እንደሆነና 185 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ እንደሆነም ተነግሯል:: ይህም እድሳት ሆስፒታሉ አገልግሎቱን በደንብ እንዲሻሻል ያደርጋል ተብሏል::

የኤካ ኮተቤ ሆስፒታል በምስራቅ አፍሪካ ግዙፍ የኒውሮ ሳይንስ ኢንስቲትዩት ለመሆን እየሰራ እንደሚገኝ ተገልጿል:

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ምንገድ ላይ

(በእውቀቱ ስዩም) በቀደም ከሆነ ቦታ ተነስቼ ወደ አልሆነ ቦታ ስራመድ...

ብፁዕ ካርዲናል አቡነ ብርሃነ ኢየሱስ በጡረታ ከኃላፊነታቸው ተሰናበቱ

የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያንና የአዲስ አበባ አገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ...

አትሌት ጉዳፍ ጸጋዬ አዲስ መግለጫ አወጣች

ታዋቂዋ አትሌት ጉዳፍ ጸጋዬ ለስፖርት ወዳጆችና ለደጋፊዎቿ ወቅታዊ መረጃ...