የእግር ኳስ ተጫዋቾች የዓመቱ ምርጥ እጩዎች ይፋ ሆኑ

Date:

የፕሮፌሽናል እግር ኳስ ተጫዋቾች ማሕበር የ2025/26 የውድድር ዓመት የዓመቱ ምርጥ እጩዎች ይፋ ሆነዋል፡፡

በዚህም አርሰናል ሦስት ተጫዋቾችን በእጩነት በማስመረጥ ቀዳሚ ሲሆን÷ ጋብሬል ማጋሌሽ፣ ዴቪድ ራያ እና ዴክላን ራይስ በእጩነት ቀርበዋል፡፡

የመድፈኞቹ ግብ ጠባቂ ዴቪድ ራያ በውድድር ዓመቱ በ19 ጨዋታዎች ግብ ሳይቆጠርበት በመውጣት የወርቅ ጓንቱን ማሸነፉ ይታወሳል፡፡

ጋብሬል ማጋሌሽ እና ዴክላን ራይስ አርሰናል የሊጉን ዋንጫ እንዲያሳካ ትልቁን አስተዋጽኦ ካበረከቱ ተጫዋቾች መካከል ተጠቃሽ ናቸው፡፡

የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የዓመቱ ምርጥ ተጫዋች ሽልማትን ያሸነፈው የማንቼስተር ዩናይትድ የመሐል ሜዳ ተጫዋች ብሩኖ ፈርናንዴዝ ሌላኛው በእጩ ዝርዝር ውስጥ የተካተተ ተጫዋች ነው፡፡

ብሩኖ 21 ለግብ የሚሆኑ ኳሶችን አመቻቶ በማቀበል በአንድ የውድድር ዓመት በሊጉ በርካታ ለግብ የሚሆኑ ኳሶችን የማቀብል ክብረ ወሰኑን የግሉ ማድረጉ አይዘነጋም፡፡

በ27 ግቦች የሊጉ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ በመሆን የወርቅ ጫማውን ያሸነፈው ኤርሊንግ ብራውት ሀላንድ እና ረያን ሼርኪ ከማንቼስተር ሲቲ በእጩነት ቀርበዋል፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...