ትምህርት ሚኒስቴር ለመምህራን ረዳት የሚሆን የሰው ሰራሽ አስተውሎት መተግበሪያ አስተዋወቀ

Date:

ትምህርት ሚኒስቴር የሁለተኛ ደረጃ መምህራንን የሥራ ጫና ለመቀነስ እና የትምህርትን ጥራት ለማረጋገጥ የሚያስችል “ኤጀንቲክ መምህር ረዳት” (Agentic AI Teacher Assistant) የተሰኘ የሰው ሰራሽ አስተውሎት መተግበሪያ አበልጽጎ በሙከራ ደረጃ ስራ ላይ አውሏል።

ይህ ቴክኖሎጂ ሙሉ በሙሉ ያለኢንተርኔት የሚሰራ ሲሆን፣ በማዕከላዊ ሰርቨር ወይም በክላውድ ቴክኖሎጂ ላይ ሳይመሰረት በአካባቢያዊ ኮምፒውተር ላይ ብቻ ተጭኖ አገልግሎት የሚሰጥ ነው።

በተጨማሪም መተግበሪያው ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ያሉትን መጽሐፍት በሙሉ ዳታሴት በመውሰድና በማስተካከል የተዘጋጀ ነው።

በመተግበሪያው ምን ምን ነገሮች ማከናወን ይቻላል ?

  • የትምህርት እቅድ (Lesson Plan) ማዘጋጀት፣
  • ደረጃቸውን የጠበቁ የፈተና ጥያቄዎችንና አሳይመንቶችን ማመንጨት፣
  • የማስተማሪያ ስልቶችን በራሱ ማቀናጀት ይችላል።

በማንኛውም ላፕቶፕ ወይም ዴስክቶፕ ኮምፒውተር ላይ ተጭኖ የሚሰራ ቀላል ሞዴልበማንኛውም ላፕቶፕ ወይም ዴስክቶፕ ኮምፒውተር ላይ ተጭኖ የሚሰራ ነውም ተብሎለታል።

በኢንተርኔት ኔትወርክ በሌላቸው የገጠርና ራቅ ያሉ አካባቢዎች ያለምንም ወጪ እና መቆራረጥ በመስራትም በከተማና በገጠር ትምህርት ቤቶች መካከል ያለውን ያጠባል ተብሎ ታምኖበታል።

በሙከራ ደረጃ የሚገኘው ይኸው መተግበሪያ ቀጣይ የማስፋፊያ ሥራዎቹ በዓለም ባንክ የገንዘብ ድጋፍ በሚንቀሳቀሰው የኢትዮጵያ የትምህርት ለውጥ ኦፕሬሽን (ETOL) ፕሮጀክት ድጋፍ እየተከናወነ ይገኛል ተብሏል።

የትምህርት ሚኒስቴር

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...