የሆላንድ ዴይረ የወተት ምርት አዲስ የሙዝ እርጎ ለኢትዮጵያ ገበያ አስተዋወቀ

Date:

በጥራት እና በአዳዲስ ስራው የሚታወቀው በኢትዮጵያ ግንባር ቀደም የወተት አምራች የሆነው ሆላንድ የወተት ተዋጽኦ የመዝ ፍራፍሬ እርጎ ምርትን በይፋ ለገብያ አቀረበ። ይሀ የሆላንድ ዴይሪ አዲስ ምርት ዛሬ በተካሄደ ልዩ የማስጀመሪያ መርሃ ግብር ላይ የሆላንድ ዴይሪ ቤተሰቦች ለሆኑት የኢንዱስትሪ መሪዎች፣ የሚዲያ ተወካዮች እና የተከበሩ እንግዶች በተገኙበት በይፋ ተዋውቋል።

የሆላንድ ዴይሪ የሙዝ እርጎ አመጠጥ የኢትዮጵያውያን ሸማቾች ጣዕምን የሚያሟላ፣ ጣፋጩ የወተት ተዋጽኦዎችን ማቅረብ ላይ ትኩረት ያደረገ ነው። ጥራቱን የጠበቀ እርጎ እና የክሬም ይዘት ያለው ከተፈጥሯዊ የሙ ፍሬ ጠፋጭነት ጋር በማዋሃድ ኩባንያው በሀገሪቱ የወተት ምርታማነትን መስፈርት በጠበቀ መልኩ ማዘጋጀቱን ቀጥሏል።

ይህ አዲስ የሙዝ እርጎ ምርት እሁን ያለውን የስትሮውበሪ (ኢንጆሪ) እና የማንጎ እርጎ አቀራረብ አይነት በሚገባ ያሟላል። ይሀም የሆላንድን አቅርቦት በሌላ ከፍተኛ ጥራት ባለው እና በአገር ውስጥ ምርቱ በንቃት እንዲስፋፋ ያደርጋል።

የሆላንድ ዴይሪ ኮሜርሺያል ዳይሬክተር ጄን-ፖል ሪዩ እንደተናገሩት “ጥራት ያለው የሆላንድ የወተት ተዋጽኦዎችን ለማቅረብ በቁርጠኝነት እንሰራለን። ይሀንንም ለማሳካት ከ4,000 በላይ ኢትዮጵያውያን ገበሬዎች ጋር ተቀራርበን በጋራ በመስራት ትኩስ እና ከፍተኛ ጥራት ያለው ወተት በማዘጋጀት ላይ ነን፡፡ ከምርጥ ወተት ደግሞ ምርጥ እርጎ እንፈጥራለን – አዲሱ የሙዝ እርጎም አንዱ ነው” ሲሉ ተናግረዋል።

የመርሃ ግብሩ ጅማሪ በምርቱ ላይ ማራኪ አቀራረብ አሳይቷል። እንግዶች አዲሱን የሙዝ እርጎ ናሙና ለመቅመስ እና የራሳቸውን አስተያየት እንዲሰጡ እድሉን አግኝተዋል። በዝግጅቱ ላይ ሆላንድ የወተት ተዋጽኦ ከአካባቢው እርስ አደሮች ጋር በመተባበር ትኩስ ወተት ለማምረት፣ በዘላቂነትን ለመስራት እና የኢትዮጵያን የወተት ኢንዱስትሪን ለመደገፍ ያለውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ልዩ ክፍልም መርሃ ግብሩ ላይ ተካቷል።

በ 425ሚ.ሊ እና 150 ሚ.ሊ መጠኖች የተዘጋጀው የሙዝ እርጎ አሁን ላይ በሀገር አቀፍ ደረጃ በየመደብሮች ውስጥ ይገኛል። ይህ የእርጎ ምርት ለቤተሰብ፣ ለአካል ብቃት አድናቂዎች እና በወተት ምርት ለመደሰት ጠፋ መንገድ ለሚፈልግ ማንኛውም ሰው አስደሳች እና ጠቃሚ መክሰስ ይሆናል።

ስለ ሆላንድ ዴይሪ የወተት ተዋጽኦ በኢትዮጵያ ውስጥ ግንባር ቀደሙ ሲሆን ከፍተኛ ጥራት የወተት ተዋጽኦዎች በማቅረብ የሚታወቅ ነው። የወተት እውቀቶችን ከኢትዮጵያ የበለፀገ የግብርና አቅም ጋር በማጣመር ታልሞ የተመሰረተው ኩባንያው ከአካባቢው አርሶ አደሮች ጋር በመተባበር ትኩስ ወተት በማምረት ዘላቂ የወተት እርባታ አሰራሮችን ይደግፋል። ሆላንድ የወተት ተዋጽኦ ምርቶች ወተት፣ እርጎ እና ሌሎች የወተት አቅርቦቶችን ያጠቃልላል፣ ሁሉም በላቀ ጥራት እና ጤና ላይ ባተኮረ ፈጠራ ይሰራሉ።

ንግስት በርታ የህዝብ ግንኙነት

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ከባለፈው  ዓመት የ130 በመቶ ብልጫ  አተረፈ

መጋቢት 30 በተጠናቀቀው የኩባንያው በጀት ዓመት 15.9 ቢሊዮን ብር...

በዕውቀቱ በታላቁ ዓለም አቀፍ ፌስቲቫል ላይ ተመረጠ

ዝነኛው ደራሲና ገጣሚ በዕውቀቱ ሥዩም በስፔን ባርሴሎና በሚካሄደው 41ኛው...

ግዮን መጽሔት ዛሬ ቅዳሜ ግንቦት 1 2018 ዓ.ም ገበያ ላይ ውሏል !!!

በኢትዮጵያ ነፃ ኘሬስ ከ25 ዓመት በላይአገልግለናል !!! -የአርበኞች አደራና የትውልዱ...

ከሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ የተላለፈ ጥሪ

በክልላችን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እያደገ የመጣው የተሳሳተ ስሌት የወለደው...