በህዘብና በዳኞች ምርጫ፤ የክብርና የእውቅና ሽልማት ከሚሰጥባቸው 19 ዘርፎች መከካል አስመጪነትና ላኪነት፣ ባንክና ኢንሹራንስ፣ አምራችነት፣ ሆቴልና ሪዞርት አንዲሁም የእድሜ ዘመን ጋዜጠኝነት የሚሉት ይገኙበታል፡፡
ስታር ዋይድ አዋርድ ከአእምሮ ጥበቃ ባለስልጣን እውቅና ያለኝ የሽልማት ድርጅት ነኝ ብሏል።
በሚቀጥለው ወር ግንቦት ላይ የሚከሄደው የሽልማት ስነ ስነስርዓቱ “ምስጋናን ባህላችን እናድርግ” በሚል መሪ ሀሳብ አንደሚካሄድ የሽልማት ደርጅቱ ስራ አስፈፃሚ አሳንቴ ስሜ ተናግረዋል፡፡
ተሸላሚዎችን ለመምረጥ ከልዩ ልዩ መስክ ዳኞች እየተመረጡ ይገኛሉ ያለው የሽልማት ዝግጅቱ፤ አሰናጅ ከለር ፉል ኢቨንት ኦርጋናይዘር ተሸላሚዎችም ከዳኞች በተጨመሪ ህዝብ ድምፅ እንዲሰጥ ይደረጋል ብሏል፡፡
አሸናዎቹም በግንቦት ወር ይታወቃሉ ተብሏል።
