አብነት ሲራጅ
የዘመናቶች ቅርሻት የትውልዶች የመቃብር ሥፍራ አንዱን ከሌላው የሚያናክስ ቢሹት የሚሰሩት ሳይሹት የሚያፈርሱት የባንዲራ ጉዳይ ዛሬም እንደ ትናንቱ ሀገራችንን ኢትዮጵያ እንደ ወረርሽኝ ሊያምሳት ተቀብሮ ያልታየውን የጀርባ የመሰለውን በሁሉም የሰው ልብ ውስጥ ያለውን የፍራቻ አፈ-ሙዙን አዙሯል፤ መረዳት ያለብን ሁላችንም ኢትዮጵያውያን ከሆንን ልናስቀድም እና ልናከብረው የምንችለው ኢትዮጵያዊ ሰው መሆናችንን ነው፤ ሌላው ከተግባር ሲተርፍ ሁሉም ነገር ከመሰረታዊ ፍላጎቶች በኋላ የሚመጡ የቅንጦት ጥያቄዎች ናቸው፡፡
በርግጥ በከተማው ተደላድሎ እና ተመቻችቶ የሚኖር አካል ስለዚህ ጉዳይ ሲነሳ የራስ ምታት ሊሆንበት ይችላል፡፡ እውነታው ግን በአንዱ ቁስል ሌላኛው እንጨት ስደድበት እንደሚባለው ነገር ነው፡፡ ነገሩ በባንዲራም ሆነ በሀገሩ ጉዳይ ስለምንም የማያውቀው የደኃው ማህበረሰብ ልጅ በስሜት እንደ ቅጠል መርገፉ ሲሆን በከተማው በየቪላ ቤቱማ ያለው ይናገረው ቋንቋ ሕሊና ቢስ ያደረገው ለሚሰራው ሥራ ሀፍረት አልባ በጥብጦ ሲግት ተዋጊ፤ የፈረደበት ሲሞት አስታራቂ መሳይ ሸምጋይ ሀቁ በሞቀ ቤት ዜና መሥራት ህሌና ላለው ካበደ መንገደኛ አጀንዳ እንደመቀበል ይቆጠራል፡፡
አጨብጭቦ መሸኘት የኳስ ተጫዋቾቹን ሞራል ይገነባው ይሆናል እንጂ አጨብጫቢው በሱ ድካም፤ ነጭ እንጥፍ ላብ፤ የምጠት ስቃይ የጭላጭ ደም፤ የሰውነት ጉዳት የውስጥ ህመም ላመል የሚሰማው ምንም የመጎዳት ስሜት የለውም፡፡
በርግጥ ኳስ ከዘጠና ሲበዛም ከመቶ ሃያ ደቂቃ በኋላ ያቆማል ያኔ ያጨብጫቢ መጨረሻው ጩኸት ወይም ዝምታ ቢሆን እንጂ ለፍልስፍና እንኳን በቅጡ የሚሆን ጥቅም አይኖረውም፡፡
በቃ ነገሩ አረረም መረረም ኳስ ጎል ስትሆን የምትጠቅመው ለተጫዋቹ ማለትም ለጎል አግቢዎቹ ነው፡፡ ጎሉ እስኪቆጠር ግን ባጨብጫቢዎች ዳንስ በተጫዋቾች ወይታ ነገሩ ሲጀመር ኳስ ከግራ ወደ ቀኝ ከቀኝም ወደ ግራ ትለጋለች፤ የኳስ ዕድሜ ሲያጥር ግን ወይ መፈንዳት ካልሆነ ግን መጣል ብቻ ነው፤ ነገሩ ከገባህ የዘመኑ ቁመራም ይሄው ነው፡፡
ለበርካታ ዘመናት እንደ ኢትዮጵያ ታሪክ ያልታደሰ ብሎም ያልተቀየረ ባንዲራ አልነበረም፤በርግጥ ለሚያውቁት ይሄ አዲስ ባይሆንም አሁን ካለው አረንጓዴ፤ ቢጫ፤ ቀይ መኃሉ በኮኮብ ሰማያዊ ቀለም እንዲሁም ካለፉት ውጪ ታላቅ ሰው ኢትዮጵያውያን እንደ ነብስያ ፃሐፊያቸው የሚያምኗቸው መሪራስ ዓማን በላይ ጥንታዊቷ የኢትዮጵያ ታሪክ በሚለው መጸሐፋቸው ላይ በአፄ ሰንደቁ ክፍለ ዘመን የኢትዮጵያ ባንዲራ አረንጓዴ፤ቢጫ እና ሰማያዊ መሐሉ ወርቃማ የኮኮብ ምልክት እንደነበረው ያወሳል፡፡
ታድያ በሳቸው ዘመን ብቻ ሳይሆን ከዛም በፊት ቀደም ብለው ባሉ የዓመት ዓለም መሪዎች የተለያዩ ባንዲራዎች እዳሏት የተለያዩ ተመራማሪያን እና ከታብያኖች ያወሳሉ፡፡
በርግጥ ለሀገራችን ኢትዮጵያ አረንጓዴ፣ ቢጫ እና ቀይ የተለያዩ አርማዎችም ቢኖሩት ትልቅ ክብር እና የህቅታ ደምም የተከፈለበት የማንነት አርማ እንደሆን ተነግሮ እስከ ተግባር ቢታወቅም ኢትዮጵያ ለሆነ ሰው ግን በጋራ እና በአንድነት እንኑር ተብሎ እንድ ስም እና መለያ እስካለን ድረስ የባንዲራ ጉዳይ ምንም ነው፡፡ ምክንያቱም ከሰው ፍጥረት የሚበልጥ ምንም ነገር የለምና፡፡
እውነተኛ ፍቅር ለሀገር ካለህ ባንዲራ ጉዳይህ የወንድምህም መዝሙር እና አርማ ዐይንህን ሊያቀላው ወይም በአዕምሮህ ልትበሳጭበት አይገባም፡፡ ነገሩ አንድ ህዝብ አንድ ሀገር ለዛውም ዲሞክራሲ ሁሉም ዜጋ ግንዛቤ አለው ተብሎ በሚታሰብበት ሃያ አንደኛው መቶ ክፍለ ዘመን የትምክት ካልሆነ አንድ የሆነን ህዝብ ይሄ አይረቤ ሀሳብ አይገዛውም፡፡
ማንም ሰው አማራ አረንጓዴ፤ ቢጫ፤ ቀይ ባንዲራ ብቻ ፤ ኦሮሞ አረንጓዴ፤ ቀይ መሐሉ የኦዳ ወይም የአርማ ምልክት ያለው እንዲሁም ነጭ፤ ቀይ፤ጥቁር ቢሆን ፍላጎቱ ስለሆነ እስልምናው ከክርስትናው እንዲሁም ሌላው ከሌላው ጋር ተከባብሮ አክብሮ እንደሚኖረው ሁሉ አክብሮ ሊከበር ይገባል፡፡ እንደ እውነቱ ከሆነ በየትኛውም የእምነት ምፅዓት እንዳለ ይታሰባል እውነታም ነው እና ምፅዓትን በምናቡ ስሎ በእምነቱን ጠብቆ በሚኖር ሰው ምፅዓት በማየደርስ ቀሪ በሆነ ከንቱ ነገር ሲፋለጥ የማይረባ ታሪክም ሲከተብ ትውልድ እንደ ወላድ ሲያምጥ መኖር የለበትም፡፡
አንድ ነን በሀገራችን በነፃነታችን የምንፈልገውን መዝሙር፤ ባንዲራ ብንሰቅልም ሁላችንም የየራሳችን አሻራ ያሳረፍንበት ስለሆነ አክብረን ልንዘክረው ቢገባን እንጂ ቂም እና ቁርሾ ባንቀልባ እንደታዘለ ዘር ብንዘራበት ለሰው መሳቂያ ለትውልድም መሳቀቂያ አስቀያሚ ትውልድ ሆነን ማለፋችን የማይቀርልን ጉዳይ ነው፡፡
ኦነግ የራሱን ባንዲራ መስዕዋትነት ከፍሎበታል፤ ፋኖ ለራሱ ማንነት የራሱን ሰውነት ገብሮበታል፤ ትግራይ፤ ሲዳማ…… በቃ ነገር ቢበዛ በአህያ አይጫን እንዲሉ ሁሉም ኢትዮጵያዊ በአንድነት ለአንድነት ሲል ራሱ መስዕዋትነትን ከፍሎበታል፡፡ ለአማራ የርስት ባንዲራ ያልሞተ ኦሮሞ፤ ትግራይ ሌላም ሌላ፤ ለኦሮምያ ባንዲራም ነገሩ ጭብጥ ባይኖረውም ሰላሳ ዓመታት በሚባለው ወቅቶች ወስጥ ያልሞተ እየሞተም ያልነበረ ብሄር ከወዴትስ መጥራት ይቻል ይሆን!
በርግጥ እንዲህ አይነት ወከባ እና ግርግር ለመፍጠር የሚሹ ሰዎች ከዚህ ቀደም የህዝብን ሀብት እና ንብረት ሲግጡ የነበሩ እየጋጡ ያሉም አካላት ኪስ ሲጎል ወይም የሚበዘበዘው የህዝብ ኃበት ወደ መመናመኑ ሲቃረብ መሆኑ ለህዝብ ጠንቋይ መቀለብ አይሻም፡፡
ታድያ ይሁንን ሲባል በየጫካው ይሄንን መሰል እኩይ ተግባር ከህዝብ ላይ ለመቀልበስ እየሰሩ ያሉ አካላት ሊኖሩ የሚችሉበት አጋጣሚ ሊኖር እንደሚችል መዘንጋት የሌለበት መሆኑ ከብቸኛው ስደተኛ የኩባዋ ንጉስ የካታሎኑ አንበሳ አማፂ ነገር ግን የመጨረሻው ግቡ ነፃ አውጪ መሆኑ በተግባር የተመሰከረለት ኸርኔስቶ ቼጉቬራን ልናስታውሰው ይገባል፡፡
በጋራ ለሞትንለት ባንዲራ በጋራ ክብር ልንሰጠው ይገባል እና ትግራይ ደሜ፤ ኦሮሞ የኔ፤ አማራ ፍላጬ…. ሌላውንም ከመውደድ ስም ካሻነው አይቀር የሀገሬው ተረት ከወደዱ አይቀር ከነ-ዓነምደር ሽንቱ ስብስብ፤ እቅፍ፤ ጥቅልል ነው እና የመስዕዋትነት ግብራችን ሲነካ የመረቀዘው ቁስል ሊፈነዳ ስለሚችል በመከባበር አንዳችን ለአንዳችን ጎፈር ሳይሆን ብሩህ ኢትዮጵያን ለማየት ዘውድ መከታ እና ከለላ ልንሆን ይገባል፡፡ ካልሆን ግን ነገሩ ጅራፍ ለራሱ ተተኩሶ ለራሱ መጬኹ ቡሄ ቢያስብለው እንጂ ለአንድነት የሚጥለው ቁብ እንደሌለው ልንገነዘብ ይገባል፡፡
