“የቤት ስራ አልሰራሽም” በሚል በአንዲት ተማሪ ላይ ተገቢ ያልሆነ ቅጣት የፈጸመችው መምህርት በቁጥጥር ስር ዋለች

Date:

በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ በሰላም በር እቅመ አንደኛና አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የ2ኛ ክፍለ ተማሪን “የቤት ስራ አልሰራሽም” በማለት ተገቢ ያልሆነ ቅጣት በፈጸመችው መምህርት ላይ እርምጃ መውሰዱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አስታውቋል።

ትውልድን ከመቅረፅ፣ የነገ ሀገር ተረካቢ ተተኪ ዜጋን ከመፍጠርና የቀለም እናት ከመሆን ባለፈ ከእናት የማይጠበቅ፤ ያለንበትን ዘመንና ወቅት የማይዋጅና የማይመጥን መሰል ድርጊት መፈጸም ተገቢ አይደለም ብሏል።

ድርጊቱ እንደተፈጸመ ጥብቅ ክትትል በማድረግ ወዲያውኑ የማጣራት ስራዎች እንዲሰሩና መምህርቷ በህግ ከለላ ውስጥ እንድትሆን መደረጉም ተገልጿል።

ጉዳዩም በህግ አግባብ እንዲታይና ፍትህ እንዲያገኝ በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ ገልጿል።

ጉዳቱ የደረሰባት ተማሪም ህክምና አግኝታ በጥሩ የጤንንነት ሁኔታ ላይ የምትገኝ ሲሆን በነገው እለትም ትምህርቷን ትጀምራላች ተብሏል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...