የድምጻዊት ኩኩ “ደጃዝማች” የተሰኘ የሙዚቃ አልበም የፊታችን አርብ ይለቀቃል

Date:

ይህ የአንጋፋዋ ድምፃዊት ኩኩ ሰብስቤ “ደጃዝማች” የተሰኘ ስምንተኛ አዲስ የሙዚቃ አልበም ላይ አስራ ሶስት ሙዚቃዎችን ይዟል።

ከእነዚህ አስራ ሶስት ሙዚቃዎች ውስጥ የስምንቱ ሙዚቃዎች ግጥምና ዜማ የድምፃዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን /ቴዲ አፍሮ / ሲሆን ሌሎቹን ሙዚቃዎች ደግሞ በግጥም ገጣሚ ይልማ ገብረአብ፣ገጣሚ መሰለ አስማማው፣ ገጣሚ ናትናኤል ግርማቸው የሰሩ ሲሆኑ ሞገስ ተካ እና ምስክር አወል ግጥምና ዜማ በመስራት በአልበሙ ላይ ተሳትፈዋል።

ከተቀሩት ስራዎች ውስጥ “ወለላዬ” የተሰኘው ሙዚቃ ደግሞ የኩኩ የድሮ ሙዚቃ ሲሆን ቴዲ ማክ እንደገና ሪአሬንጅ /Re Arrange/ አድርጎ የሰራው ሙዚቃ ነው።

የድምፃዊት ኩኩ ሰብስቤ ” ደጃዝማች” በተሰኘው አዲስ አልበም ላይ ስመጥር የሆነ የሙዚቃ ባለሞያዎች የተሳተፉበት ሲሆን የሙዚቃ አቀናባሪው አቤል ጳውሎስ ዘጠኙን ሙዚቃዎች በማቀናበር እንዲሁም አስራ አንዱን ሙዚቃዎች ሚክስ በማድረግ ተሳትፏል።

ሁለቱን ሙዚቃዎች አሬንጅ ያደረገው ማሩ ዓለማየሁ ሲሆን ሙዚቀኛ ያሬድ ተፈራ፣ ሙዚቀኛ አክሊሉ ወ/ዩሐንስ (ጆኒ ሳክስ) እና ሙዚቀኛ ዘሪሁን በለጠ በሳክስፎን፣ግሩም መዝሙር እና ሳሙኤል አሰፋ በጊታር ተሳትፈዋል።

“ደጃዝማች”ን ሙሉውን አልበም ማስተር ሳውንዱን /Sound Mastering/የሰራው ኪሩቤል ተስፋዬ ነው።

“ደጃዝማች” የተሰኘ ስምንተኛ አልበም የፊታችን አርብ ሚያዚያ 24 ቀን 2017 ዓ.ም በራሷ ዩቲዩብ ቻናል ይለቀቃል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...