የኢትዮጵያ ጤና ባለሙያዎች ማኅበር ፕሬዝዳንት የሆኑት አቶ ዮናታን ዳኛው ዛሬ በጸጥታ ኃይሎች መታሰራቸውን ማኅበሩ አስታውቋል።
ማኅበሩ እንደገለጸው ፕሬዝዳንቱ የታሰሩት የጤና ባለሙያዎች እያነሷቸው ላሉት ጥያቄዎች ድምጽ በመሆናቸው ነው እንጂ በግል ጉዳያቸው አይደለም።
አቶ ዮናታን ከመታሰራቸው በፊት ለባልደረባቸው በስልክ እንደተናገሩና ለምርመራ እንደሚፈለጉ እንደተነገራቸው ማኅበሩ ገልጿል።
ሆኖም ዛሬ ከቤታቸው ተወስደው መታሰራቸውን ቤተሰቦቻቸው አሳውቀዋል።
የኢትዮጵያ ጤና ባለሙያዎች ማኅበር ፕሬዝዳንቱ መታሰራቸው እጅግ እንዳሳሰባቸው በመግለጫው ያሳወቀ ሲሆን በቀጣይ ምን ሊፈጠር እንደሚችልም ያላቸውን ስጋት ገልጸዋል።
