የብሪታንያ የፖሊቲካ ፓርቲዎች መራጮቻቸውን እንዴት አሳዘኑ?

Date:

የፖለቲካ ፓርቲዎች ብዙ ጊዜ ትልቅ ተስፋን ይዘው ወደ ስልጣን የሚመጡ ሲሆን የስልጣን ወንበራቸው ላይ ሲቀመጡ ቃል የገቡትን ይረሱታል።

ይህ ቃልን ያለመፈፀም አባዜ ሌበርም ሆነ ኮንሰርቫቲቭ ፓርቲ የተካኑበት ነው።

ኮንስርቫቲቭ ፓርቲ (ቶሪ) – የተሰበረ ቃል ኪዳን ፓርቲ

ግብሮች፦ “አዲስ ግብር አይኖርም ” (ከአዳዲስ ግብሮች በስተቀር)

🔥 ቃል የተገባው፦ ቦሪስ ጆንሰን እ.ኤ.አ በ2019 ግብር እንደማይጨምር ማረጋጋጫ ሰጥተው ነበር።

💀 እውነታው፦ እ.ኤ.አ በ2021 ብሔራዊ ኢንሹራንስ ጨምሯል፤ በተጨማሪም የግብር ክፍያዎች ሠራተኞች የሚያገኙት ገቢ እንዲቀንስና ፓርቲው የገባውን የ “አነስተኛ ታክስ” ቃል እንዲያፈርስ አድርጓል።

ብሔራዊ የጤና አገልግሎት (ኤንኤችኤስ)፦ የሆስፒታሎችን ትግል ያስቀጠለው የገንዘብ ድጋፍ

🔥 ቃል የተገባው፦ በ2023-24 ለኤንኤችኤስ ተጨማሪ 34 ቢሊዮን ፓውንድ ይመደባል፡፡

💀 እውነታው፦ የገንዘብ ድጋፉ በቂ ባለመሆኑ ምክንያት ኤንኤችኤስ ለከፍተኛ የታካሚዎች ወረፋ፤ የመሠረተ ልማት መዳከም እና ታሪካዊ አድማዎች ተጋልጧል።

ኢሚግሬሽን፦ “እንቆጣጠረዋለን” (ከዛም ሳይፈጽሙ መቅረት)

🔥 ቃል የተገባው፦ ብሬግዚት ስደትን ይቀንሳል እንዲሁም ደህንነታቸው የተጠበቀ ድንበሮች ይኖራሉ።

💀 እውነታው፦ ፍልሰት ወደ 745 ሺህ ከፍ ብሏል፣ የሩዋንዳ እቅድ ከሽፏል፣ በተጨማሪም ወግ አጥባቂው ፓርቲ ብሬግዚትን አስመልክቶ የገባቸውን ዋና ዋና ቃሎች መፈፀም አልቻለም።

አየር ንብረት፦ የአረንጓዴ ቃል ኪዳኖች፤ ግን የበለጠ ብክለት

🔥 ቃል የተገባው፦ በ2050 የካርቦን ልቀትን ወደ ዜሮ መቀነስ።

💀 እውነታው፦ ሱናክ የነዳጅ መኪና እገዳን አዘግይተዋል፣ አዲስ የነዳጅ ዘይት ቁፋሮን አፅድቀዋል እንዲሁም ከአየር ንብረት እርምጃ  ይልቅ የቅሪተ አካል ነዳጅ ጥቅሞችን ደግፈዋል።

የሌበር ፓርቲ – የተተዉ መርሆች ፓርቲ

🔥 ቃል የተገባው፦ ቶኒ ብሌር እ.ኤ.አ በ1997 “ለትምህርት የሚከፍል ክፍያ አይኖርም”።

💀 እውነታው፦ በ1998 በዓመት አንድ ሺህ ፓውንድ የትምህርት ክፍያ የተጀመረ ሲሆን አሁን ከ9 ሺህ 250 በልጦ ተማሪዎች የከፍተኛ ዕዳ ተሸካሚ ሆነዋል፡፡

የኢራቅ ጦርነት፦ ጦርነት ያወጁ “አሸማጋዮች”

🔥 ቃል የተገባው፦ ሌበር የዲፕሎማሲ ፓርቲ ነው።

💀 እውነታው፦ ብሌር ብሪታንያን በውሸት ላይ የተመሠረተ ሕገ-ወጥ ጦርነት ውስጥ በመክተት በመካከለኛው ምስራቅ ለሚሊዮኖች ሞት እና አለመረጋጋት መንስዔ ሆነዋል።

መኖሪያ ቤት፦ “ተጨማሪ ማህበራዊ ቤቶች” (ከዚያም ቤቶቹን መሸጥ)

🔥 ቃል የተገባው፦ ብዙ ማህበራዊ ቤቶች ይገነባሉ።

💀 እውነታው፦ ብሌር እና ብራውን ጉዳዩን ወደ ግሉ ዘርፍ በማዞር የቤት ፍላጎቶችን ማሟላት ተስኗቸው አሁን ላይ ለተፈጠረው ቀውስ አስተዋፅዖ አድርገዋል።

ኢኮኖሚ፦ ከኮርቢን ራዕይ እስከ የስታርመር ክሽፈት

🔥 ቃል የተገባው፦ የባቡር ሀዲዶችን፣ መገልገያዎችን ብሔራዊ ማድረግ እና ሀብታሞችን ግብር ማስከፈል (2019)።

💀 እውነታው፦ ስታርመር ሌበር የግራ ዘመም ማሻሻያዎችን ወደ ለዘብተኝነት በመቀየር ለኮርፖሬሽኖች ምቹ የሆኑ ፖሊሲዎችን እንዲከተል መርጠዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር የተዘጋጀው የመጀመሪያው አህጉራዊ የሪል ስቴት ኤግዘቢሽን ተከፈተ

በኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር አዘጋጅነት የመጀመሪያው አህጉራዊ የሪል...

በሊባኖስ እና በእሰራኤል የተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት ተራዘመ

ትራምፕ በሊባኖስ እና በእሰራኤል መካከል የተደረሰው የተኩስ አቁም በሦስት...

ከ 50 ሚሊዮን በላይ መራጮች በማንዋልና በዲጂታል ተመዝግበዋል

ከየካቲት 28_መጋቢት 28 የመራጮች ምዝገባ ሲካሄድ እንደነበር ይታወቃል። በተለያዩ ጉዳዮች...

በኦሮሚያ ክልል የ4.5 ሚሊዮን ዶላር የአስቸኳይ ጊዜ ድጋፍ ፕሮጀክት ይፋ ተደረገ

ፈያ ኢንተግሬትድ ዴቬሎፕመንት ኦርጋናይዜሽን በኦሮሚያ ክልል የሚከሰቱ የበሽታ ወረርሽኞችን...