በ17 ዓመቱ 5 ዋንጫዎችን ያነሳው ድንቅ የእግር ኳስ ተጫዋች

Date:

የእግር ኳሱ ኮከብ ሊዮኔል ሜሲ ባደገበት ላሜሲያ አካዳሚ ተምሮ ሜሲን እያደነቀና እንደ አርአያ በመከተል ወደ እግር ኳስ ዓለም የገባው ላሚን ያማል አሁን የዘመኑ ኮከብ ለመሆን ጉዞውን ጀምሯል።

ባርሴሎና ትላንት ምሽት እስፓኞልን 2-0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ለ28ኛ ጊዜ የላሊጋ ዋንጫን ሲያነሳ ላሚን ያማል የመክፈቻውን ግብ አስቆጥሯል። በተጨማሪም ለሁለተኛው ጎል አመቺ ኳስ በማቀበል የግብ ዕድል ፈጣሪ ሆኗል።

ክርስቲያኖ ሮናልዶ በማድሪድ ሁለት የላሊጋ ዋንጫዎችን ለማንሳት የፈጀበትን 9 ዓመታት ያህል ጊዜ ላሚን ያማል በ2 ዓመታት ውስጥ ማሳካት ችሏል።

በዚህ የውድድር ዓመት ባደረጋቸው 45 ጨዋታዎች 17 ግቦችን ከመረብ ያሳረፈ ሲሆን ለ25 ግቦች አመቺ ኳሶችን አመልክቷል።

አዲሱ የእግር ኳስ ኮከብ ያማል በዚህ ዓመት ባርሴሎና 3 ዋንጫዎችን እንዲያሸንፍ ትልቅ ሚና ከተጫወቱ ተጫዋቾች መካከል ዋነኛው ነው።

በ2024/25 የውድድር ዓመት የላሊጋውን፣ የኮፓ ዴል ሬይ እና የስፔን ሱፐር ካፕ ዋንጫዎችን በማንሳት የሶስትዮሽ ድልን አስመዝግቧል።

የስፔን ብሔራዊ ቡድን የ2024 የአውሮፓ ሻምፒዮናን ሲያነሳ የቡድኑ ወሳኝ ተጫዋች ነበር።

በዓለም የእግር ኳስ ታሪክ በ17 ዓመቱ 5 ዋንጫዎችን በማንሳት የመጀመሪያው ተጫዋች እንደሆነ እየተነገረ ነው።

በ17 ዓመቱ 2 የላሊጋ ዋንጫ፣ 1 የኮፓ ዴል ሬይ ዋንጫ፣ 1 የስፔን ሱፐር ካፕ ዋንጫ እና 1 የአውሮፓ ሻምፒዮና ዋንጫዎችን አሸንፏል።

ይህ ወጣት ተጫዋች በግሉ በርካታ ሽልማቶችን ያገኘ ሲሆን ከእነዚህም መካከል፡-

ጎልደን ቦይ (በአውሮፓ ምርጥ ወጣት ተጫዋች – 2024)
የላሊጋው ኮከብ ወጣት ተጫዋች (2024)
ራይሞንድ ኮፓ ሽልማት (በዓለም ከ21 ዓመት በታች ምርጥ ተጫዋች – 2024)
የዓለም ምርጥ ወጣት ተጫዋች (2024)
በዓለም ኮከብ ወጣት ተጫዋች (2023)
የአውሮፓ ኮከብ አዳጊ ተጫዋች (2024)
የላውረስ የዓመቱ ምርጥ ግኝት (2025)
የዓለም ምርጥ ብሔራዊ ቡድን፣ የአውሮፓ ምርጥ ቡድን እና የዓለም ምርጥ ወጣት ቡድን አባል (ከስፔን ብሔራዊ ቡድን ጋር – 2024) ይጠቀሳሉ።

ሜሲ በሰለጠነበት አካዳሚ አድጎ ሜሲን በመተካት አሁን በስፔን ብቻ ሳይሆን በአለም እግር ኳስ አዲስ ክስተት ለመሆን በቅቷል።

የባሎንዶር ሽልማትንም ሊያገኝ ይችላል የሚሉ ግምቶች እየተሰሙ ነው።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የተፈናቀሉ ዜጎች በተጠለሉበት አካባቢ በቋሚነት መኖር የሚያስችላቸው 

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን የዳሰነች ወረዳ ከበኦሞ...

ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ 11ኛውን የኃይሌ ሆቴልና ሪዞርት በደብረ ብርሃን ከተማ አስመረቀ

ታዋቂው አትሌትና ባለሀብት ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ፣ በደብረ ብርሃን ከተማ...

በኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር የተዘጋጀው የመጀመሪያው አህጉራዊ የሪል ስቴት ኤግዘቢሽን ተከፈተ

በኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር አዘጋጅነት የመጀመሪያው አህጉራዊ የሪል...

በሊባኖስ እና በእሰራኤል የተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት ተራዘመ

ትራምፕ በሊባኖስ እና በእሰራኤል መካከል የተደረሰው የተኩስ አቁም በሦስት...