በሀገሪቱ የሚስተዋለው “ስር የሰደደ የሰላም እጦት” ምላሽ እንደሚገባው የኢትዮጵያ ሶሻል ዴሞክራቲክ ፓርቲ (ኢሶዴፓ) ጠየቀ።
ፓርቲው ዛሬ ባወጣው መግለጫው ከትግራይ ጦርነት ትምህርት በመውሰድ አሁን እየተካሄደ ያለው ጦርነት “በሰላማዊ መንገድ” መፍትሄ እንዲበጅለት ጠይቋል።
በጦርነት “የሰው ነብስ እየጠፋ” እንደሆነ ያመለከተው ኢሶዴፓ “ሁሉን አካታች ውይይቶች እና ሃቀኛ ድርድሮች” እንዲደረጉ አሳስቧል።
ከሰሞኑ በጤና ባለሞያዎች እያቀረቡ ያሉት የደሞዝ እና ሌሎችም ጥያቄዎቻቸው በተገቢው መንገድ ምላሽ እንዲሰጣቸው ፓርቲው ጠይቋል።
ኢሶዴፓ ሃገሪቱ ያጋጠሟት፣ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እንዲሁም ማህበራዊ ጥያቄዎች እንደ አግባቡ በሰላማዊ መንገድ ሳይፈቱ መቅረታቸው ወደ ኃይል ርምጃ መገባቱ የሃገሪቱን ህልውና እየተፈታተነ እንደሆነ ማስተዋሉን አመልክቷል።
(ሀገሬ ቴቪ)
