በረሀብ እና በአልሚ ምግብ እጥረት ምክንያት የሞቱ ተፈናቃዮች ቁጥር 992 መድረሱ ተነገረ

Date:

በትግራይ ክልል በሽሬ ከተማ በሚገኙ መጠለያ ጣቢያዎች ውስጥ ከሚገኙ ተፈናቃዮች መካከል በአልሚ ምግብ እጥረት እና በርሃብ ምክንያት የሞቱት ተፈናቃዮች ቁጥር 992 መድረሱን የኢትዮጵያ እንባ ጠባቂ ተቋም የትግራይ ክልል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት አስታውቋል።

የቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቱ ኃላፊ ጸሐዬ እምባዬ በ1 ዓመት ጊዜ ውስጥ የደረሰው ሰብአዊ ኪሳራ ተጠንቶ መጠናቀቁን እና ቁጥሩም ከ550 ወደ 992 ከፍ ማለቱን  ተናግረዋል። 

በአሁኑ ሰዓት በሽሬ ከተማ እና በአካባቢዋ ከ250 ሺሕ በላይ ተፈናቃይ በርሃብና በሽታ እየተሰቃዩ መሆኑን አንስተው፤ የሚመለከተው አካል ትኩረት እንዲሰጣቸው ጥሪ አቅርበዋል።

በሽሬ ከተማ ብቻ ሳይሆን በአጠቃላይ በክልሉ የሚገኙት ተፈናቃዮቹ በ2015 ዓ.ም. ጥር ወር አካባቢ ጀምሮ የሚሰጣቸው ሰብአዊ እርዳታ በመቋረጡ ምክንያት፤ ተፈናቃዮች ለርሃብ እና ለበሽታ መዳረጋቸውን ተናግረዋል።

በክልሉ የዓለም የምግብ ፕሮግራም (WFP) ለእያንዳንዱ ተፈናቃይ 15 ኪ.ግ. ዱቄት እርዳታ እንደሚሰጥ ቢያሳውቅም እየተሰጠ ያለው ግን 9 ኪ.ግ. መሆኑን የገለጹት ኃላፊው፤ የሚላከው የእርዳታ እህል ከሚያስፈልገው ጋር ልዩነት አለው” ብለዋል።

በአጠቃላይ በትግራይ ክልል ከሱዳን የተመለሱ እና ወደ ቀያቸው ተመልሰው በጸጥታ ችግር ምክንያት IDP በተባለ ተቋም ሥር ያሉትን ሳይጨምር 970 ሺሕ በላይ ተፈናቃዮች በችግር ውስጥ መሆናውን ኃላፊው አስታውቀዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...