ደቡብ ሱዳን ከኢትዮጵያ ጋር በምትዋሰንባቸው አካባቢዎች ያለው ግጭት መባባሱ ተገለጸ

Date:

ድንበር የለሹ የሃኪሞች ቡድን (MSF) ደቡብ ሱዳን ከኢትዮጵያ ጋር በምትዋሰንባቸው አካባቢዎች ያለው ግጭት በመባባሱ የህክምና አገልግሎቱን ወደ ጋምቤላ፤ ማታር ማምጣቱን ገልጿል።

ከዚህ በፊት አገልግሎቱን በርቤይ በምትባል የድንበር ከተማ ይሰጥ እንደነበረ የገለጸው ቡድኑ ግጭቱ በመባባሱ አገልግሎቱን በጋምቤላ ክልል፤ ኑዌር ዞን፤ ማታር ለማዘዋወር መገደዱን ገልጿል።

ወደ በርቤይ ተፈናቅለው መጥተው የነበሩ ደቡብ ሱዳናዊያንም ወደ ማታር ዳግም መሰደዳቸውን ቡድኑ ሲገልፅ “የጋምቤላ ክልል በኮሌራ በሽታ እና ስደተኞችን በመቀበል ተጨናንቃለች” ብሏል።

በኢትዮጵያ በኩል ባለችው በርቤይ ድንበር የለሽ የሀኪሞች ቡድን ከ1200 በላይ የኮሌራ ተጠቂዎችን ማከሙን ሲገልፅ በደቡብ ሱዳን የላይኛው ናይል ግዛት ግጭት ከተከሰተ በኋላ በበርቤይ 217 በጦርነቱ የቆሰሉ ሰዎችን ማከሙንም ቡድኑ አስታውቋል።

ቡድኑ በፈረንጆቹ ግንቦት 12 ድንበር የተሻገረ የተኩስ ልውውጥ መደረጉንም ገልጿል።

ተፈናቃዮቹ የአየር ላይ ጥቃቶችን ሸሽተው መምጣታቸውን ሲገልፁ  በአሁኑ ጊዜ በጋምቤላ ክልል ማታር ከ35,000- 85,000 ሰዎች ተፈናቅለው እንደሚገኙም ተነግሯል።

የሂኪሞች ቡድኑ የአካባቢው መሰረተ ልማቶች ማስተናገድ ከሚችሉት በላይ እያስተናገዱ ነው ያለ ሲሆን፤ ምርመራ ከሚደረግላቸው ሰዎች መሃልም 40 በመቶዎቹ የወባ በሽታ ተጠቂ ናቸው ብሏል።

ስደተኞቹ የውሃ እጥረትን ጨምሮ በርካታ ችግሮች እያጋጠሟቸው ነው ያለው ቡድኑ ወሳኝ የሚባሉ የጤና አገልግሎቶቹንም ከበርቤይ ወደ ማታር ማዘዋወሩን አስታውቋል።

በርቤይ በኢትዮጵያ እና ደቡብ ሱዳን ድንበር ላይ የምትገኝ አዋሳኝ የድንበር ከተማ ስትሆን የደቡብ ሱዳን ስደተኞችም ዋነኛ መዳረሻ ነበረች።

የሃኪሞቹ ቡድን እንደገለፀው በደቡብ ሱዳን መንግስት እና በታጣቂዎቹ መካከል የተፈፀሙ የተኩስ ልውውጦች ድንበር ተሻግሮ በበርቤይ ያሉ ሰዎችን የጎዳ ሲሆን በተፈጠረበት ስጋት የተነሳም ወደ ማታር አገልግሎቱን ማዞሩን ገልጿል።

ስደተኞቹም ወደ በርቤይ ከመጡ በኋላ ዳግም በስጋት ወደ ማታር መሰደዳቸው ተገልጿል።

የሃኪሞች ቡድን አለም አቀፍ ተቋማት ድጋፋቸውን እንዲያደርጉም ጠይቋል።

በደቡብ ሱዳን በታጣቂዎች እና በመንግስት ወታደሮች መካከል ግጭት ከተፈጠረ የሰነባበተ ሲሆን ግጭቱ ከኮሌራና ወባ በሽታ ጋር ተዳምሮ ከባድ ቀውስን እየፈጠረ ይገኛል።

የደቡብ ሱዳን መንግስት ባለፈው ሳምንት ከኢትዮጵያ ጋር የምዋሰንባቸውን አካባቢዎች ከታጣቂዎቹ ነፃ አድርጌ ተቆጣጥሬያለሁ ቢልም በአካባቢዎቹ አሁንም ውጊያዎች መኖራቸው ተዘግቧል።

tikvah

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...