የስምንት ሀገራት ልዑካን በትግራይ ማሰልጠኛ ማዕከሉን  ጎበኙ

Date:

የአውሮፓ ህብረት እና አሜሪካ ጨምሮ የስምንት ሀገራት ልዑካን በትግራይ ክልል የቀድሞ ተዋጊዎችን ወደ ህብረተሰቡ የመቀላቀል ተግባርን ለማከናወን በሚል የተቋቋሙት የተሃድሶ ስልጠና የሚሰጥባቸውን ማዕከላት መጎብኘታቸው ተገለጸ።


የአሜሪካ፣ የአውሮፓ ህብረት፣ የካናዳ፣ እንፍሊዝ፣ ጃፓን፣ ስዊዲን፣ ፈረንሳይ እና ዴንማርክ ልዑካን ጉብኝት ያካሄዱት በሚያዚያ ወር 2017 ዓ.ም ስራ በጀመረው አዲብራክ ማሰልጠኛ ተቋም መሆኑን ከትግራይ ቴሌቪዢን ያገኘነው መረጃ ያሳያል።


በሚያዚያ ወር ስራ የጀመረው የማሰልጠኛ ማዕከሉ አምስት ሺ የሚጠጉ የቀድሞ ተዋጊዎችን ወደ ህብረተሰቡ መቀላቀሉን አስተባባሪው አቶ አሳይ ገ/መድህን መግለጻቸውን ዘገባው አስታውቋል።
በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የልማት ፕሮግራም የቀድሞ ተዋጊዎች መልሶ ማቋቋም ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሚስተር ባሲል የጉብኝቱ አላማ ተዋጊዎችን መልሶ ወደ ህብረተሰቡ የመቀላቀሉ ሂደት በምን ደረጃ ላይ እንዳለ ለመታዘብ ነው ብለዋል።


ሂደቱም በሁሉም ባለድርሻ አካላት ተሳትፎ እና ትብብር  በሚገባ እየተካሄደ መሆኑን ለመረዳት ችለናል ብለዋል።
ተዋጊዎቹን ወደ ህብረተሰቡ በመቀላቀል ሂደቱ ላይ ከመጀመሪያው ከዕቅዱ ጀምሮ እስከ በጀት መመደብ እና ትግበራው መቆጣጠር ድረስ ፈንድኑን የሰጡ ሀገራት እያደረጉት ያለው ድጋፍ ቀላል አይደለም ሲሉ ገልጸዋል።


በተጨማሪም የፌደራል መንግስቱ እና የክልሉ ጊዜያዊአስተዳደርም እንዲሁም የተሃድሶ ኮሚሽን እያበረከቱት ያለው አስተዋጽኦ በመታዘብ የስልጠና ማዕከሉ እንዴት መሻሻል እንዳለበት እንወስናለን ሲሉ ተደምጠዋል።
ፕሮግራሙ እንዲሳካ 11 ለጋሽ ሀገራት በገንዘብ እየደገፉ ይገኛሉ ያሉት ዳይሬክተሩ የተሃድሶ ኮሚሽን እያከናወናቸው ያሉ ስራዎችም ውጤት እያመጠ መሆኑን ለመገንዘብ ችለናል ብለዋል።


በተያዘው አመት ሚያዚያ ወር ላይ ስራ የጀመረው የአዲበራክ ካምፕ አስተባባሪ የሆኑት አቶ አሳይ ገ/መድህን “በየሳምንቱ ሁለት መቶ የሚሆኑ የቀድሞ ተዋጊዎች ስልጠና ወስደው ከካምፑ እንደሚወጡ” መግለጻቸውነ ጠቁሟል።
ማዕከሉ ስራ ከጀመረበት ከሚያዚያ ወር 2017 ዓ.ም ጀምሮ ደግሞ ከአራት ሺ 800 በላይ የቀድሞ ተዋጊዎችን በማሰልጠን ወደ ህብረተሰቡ እንዲቀላቀሉ ማድረጉን ጠቁመዋል።


በትግራይ 75,000 የቀድሞ ተዋጊዎችን ትጥቅ የማስፈታት እና ወደ ማህበረሰቡ የመቀላቀል ሂደት በህዳር 12 ቀን 2017 በይፋ መጀመሩ ይታወቃል።
የብሔራዊ ተሃድሶ ኮምሽን በትግራይ ክልል እስከ ሰኔ ወር ድረስ እንደሚጠናቀቅ በተገለጸው በመጀመሪያ ዙር ለ75 ሺህ የቀድሞ ተዋጊዎች የተሃድሶ ስልጠና በመስጠት ወደ ሰላማዊ ሕይወት ለመመለስ ቢያቅድም እስከ አሁን የተመለሱት 17 ሺህ ብቻ መሆናቸውን ማስታወቁን ሚያዚያ 20 ቀን 2017 ዓ.ም ባቀረብነው ዘገባ መመላከቱ ይታወሳል።


በተያዘው አመት 2017 ዓ.ም ህዳር ወር አጋማሽ በብሔራዊ ተሃድሶ ኮምሽን ተጀምሮ የነበረው እንስቅስቃሴ ብዙ ሳይዘልቅ ለወራት ተቋርጦ መቆየቱን የብሔራዊ ተሃድሶ ኮምሽን ኮምሽነር ተመስገን ጥላሁን መናገራቸውን ዘገባው አካቷል። በዚህም በክልሉ የነበረው ፖለቲካዊ አለመረጋጋት እንዲሁም ከትጥቅ ርክክብ ጋር በተያያዙ ምክንያቶች ተጀምሮ የነበረው ሂደት ተደናቅፎ እንደነበረ ኮሚሽነሩ ተናግረዋል።


በሌላ ዜና ብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን በትግራይ ክልል “በአንዳንድ ቴክኒካዊ እና ፖለቲካዊ” ምክንያቶች ተቋርጦ የነበረውን የቀድሞ ተዋጊዎችን የማረጋገጥ፣ ዲሞቢላይዝ የማድረግ፣ የመመዝገብና የተሃድሶ ስልጠና በመስጠት ወደ ማህበረሰቡ የመቀላቀል ሥራ በሚያዚያ ወር 2017 ዓ.ም መጨረሻ ሳምንት በመቐለ እና በዕዳጋ ሀሙስ ማዕከላት እንደገና እንደሚጀምር ማስታወቁን መዘገባችን የታወሳል። 

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር የተዘጋጀው የመጀመሪያው አህጉራዊ የሪል ስቴት ኤግዘቢሽን ተከፈተ

በኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር አዘጋጅነት የመጀመሪያው አህጉራዊ የሪል...

በሊባኖስ እና በእሰራኤል የተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት ተራዘመ

ትራምፕ በሊባኖስ እና በእሰራኤል መካከል የተደረሰው የተኩስ አቁም በሦስት...

ከ 50 ሚሊዮን በላይ መራጮች በማንዋልና በዲጂታል ተመዝግበዋል

ከየካቲት 28_መጋቢት 28 የመራጮች ምዝገባ ሲካሄድ እንደነበር ይታወቃል። በተለያዩ ጉዳዮች...

በኦሮሚያ ክልል የ4.5 ሚሊዮን ዶላር የአስቸኳይ ጊዜ ድጋፍ ፕሮጀክት ይፋ ተደረገ

ፈያ ኢንተግሬትድ ዴቬሎፕመንት ኦርጋናይዜሽን በኦሮሚያ ክልል የሚከሰቱ የበሽታ ወረርሽኞችን...