ሃይንከን ኢትዮጵያ አዲስ ሜትር ታክሲን የትግበራ አጋር በማድረግ አሽከርካሪዎች ከጠጡ በጭራሽ እንዳይነዱ ግንዛቤን የሚያስጨበጥ “በልክ በአግባብ በሀላፊነት – አራዳ ከጠጣ የማይነዳ” የሚል ዘመቻውን ሰኔ 5 ቀን 2017 ዓ/ም በይፋ አስጀመረ፡፡
ድርጅቱ “በልክ”ን በመስቀል ፍላዎር አደባባይ ያስጀመረው በ50 የአዲስ ሜትር ታክሲዎች ላይ የሄንኑ መልዕክቱን በመለጠፍ ሲሆን፤ መልዕክቱ ምንም አይነት መጠጥን የሚያበረታታም ይሁን ማን መልዕክቱን እንደአስተላለፈው የሚገልጽ ምልክት የለውም።
“ጠጥቶ ማሽከርከር የሚያስከትለውን አደጋ በመገንዘብ እንደ አንድ ሃላፊነት እንደሚሰማው ድርጅት ያስጀመርነው ይህ ዘመቻ በ50 ታክሲዎች ላይ መልዕክቱን በመለጠፍ ለ6 ወራት እንዲቆይ እናደርጋለን” ያሉት የሃይንከን ኢትዮጵያ የሴስቴይነብሊቲ የውጭና መንግስታዊ ጉዳዮች ኃላፊ የሆኑት አቶ ፍቃዱ በሻህ ይህ መልዕክት ታክሲዎቹ ተዘዋውረው በሚሰሩበት በአዲስ አበባና በዙሪያዋ ባሉ ከተሞች በቀን ከ2 ሚልዮን በላይ ህዝብ ይመለከተዋል ብለዋል፡፡
ሃይንከን ኢትዮጵያ ከዚህም ጎን ለጎን አልኮል መጠጥን በሃላፊነት መጠቀም በሚለው ዘመቻው ስር እድሜያቸው ከ21 ዓመት በታች ያሉ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች No for Underage Drinking “አልኮል አልቀምስም” የሚል ስልጠናም ይሰጣል፡፡ የሃይንከን ምንም አሻራ ሳይገኝ ስልጠናውን የሚሰጡለት መንግስታዊ ያልሆኑ የትግበራ አጋሮቹ ሲሆኑ፤ መርሃ-ግብሩ እስከ አሁን በመላው አገሪቱ ባሉ 11 ዩኒቨርሲቲዎች ተካሂዷል፡፡
የበልክ መርሀ-ግብር የሃይንከን ኢትዮጵያ ማኔጂንግ ዳይሬክተር የሆኑት ባርት ዲ ኬኒንክ፣ የሴስቴይነብሊቲ የውጭና መንግስታዊ ጉዳዮች ኃላፊ አቶ ፍቃዱ በሻህ፣ የአዲስ ሜትር ታክሲ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ፍቃዱ ኃይሉ እና የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን ተወካይ አቶ ኢሳ አሰፋ እንዲሁም የትራፊክ ፖሊስ ተወካዮች በጋራ በመሆን ነው፡፡
