በዓለም አቀፍ ደረጃ በየዓመቱ 150 ሚሊዮን ሴቶች ወሲባዊ ጥቃት ይደርስባቸዋል

Date:

በኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች ሴት ልጅ ከወንድ ቤተሰብ  በሚመጣ ሀብት ማለትም   ከብት እንዲሁም ወርቅ  እንደየ አካባቢው  የመቀየር  ስርዓት መኖሩ ተነግሯል።

የሴት ልጅ ላይ የሚደርስ ጾታዊ  ጥቃት የሰብዓዊ  መብት ጥሰት ከመሆኑ በላይ በኢትዮጵያ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሴቶችን ወደ ተለያዩ ችግሮች የሚከት ጤናን  የሚጎዳ  እና  ስር የሰደደ ችግር መሆኑ ተገልጿል ።

በተለያዩ አካባቢዎች የሴት ልጅ ጥቃት ከባህል አኳያ የሚደርስ ሲሆን  ከእነዚህ መካከል የልጅነት ጋብቻ ፣ የሴት ልጅ ግርዛት በተለያዩ አካባቢዎች የሚዘወተሩ እና እንደ ባህል የሚታዩ ልምዶች መሆናቸው ተጠቁሟል።

በተለያዩ አካባቢዎች ሴት ልጅ ከወንድ ቤተሰብ  በሚመጣ  ሀብት ማለትም  ከብት እንዲሁም ወርቅ  እንደየ አካባቢው የመቀየር  ስርዓት መኖሩ ተነግሯል።

በዚህም ሚስት ለማግኘት የሚበቃ ከብት የሌላቸው የወንድ ቤተሰቦች በአንዳንድ አካባቢዎች ትዳር ለማግኘት በመቸገራቸው  ወደ ሌላ አካባቢዎች እንደሚሰደዱ በፕላን ኢትዮጵያ  የኮሙኒኬሽን ክፍል ሃላፊ የሆኑት ዶክተር ምስክር  ጌታሁን ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።

በኢትዮጵያ ያለ እድሜ ጋብቻ ፣ጾታዊ  እኩልነት፣ እንዲሁም በትዳር ውስጥ በኢኮኖሚ የሚደርሱ ጫናዎች  እና ጥቃቶች ትኩረት  ሊሰጣቸው የሚገባ ጉዳዮች ናቸው ተብሏል።  በዓለም ላይ ከሶስት ሴቶች አንዷ በህይወት ዘመኗ  አካላዊ ወይም  ለስነልቦናዊ ለሆነ ጾታዊ ጥቃት ትጋለጣለች ።

በአፍሪካ ከስምንት ሴቶች መካከል አንዷ ከ15 ዓመት በታች እያለች እንደምትዳር ተገልጿል ። በ2016 የወጣው መረጃ እንደሚያሳየው በአፍሪካ 25 በመቶ የሚሆኑ ሴቶች  አካላዊ ጥቃት የሚደርስባቸው ሲሆን 36 በመቶ የሚሆኑት ደግሞ ስነልቦናዊ ጥቃት ይደርስባቸዋል ።

በዓለም አቀፍ ደረጃ በየዓመቱ  150 ሚሊዮን ሴቶች ወሲባዊ ጥቃት፣  200 ሚሊዮን የሴት ልጅ ግርዛት እና 700 ሚሊዮን ያለእድሜ ጋብቻ ይፈጸምባቸዋል ። 

በተጨማሪም በየቀኑ  137 ሴቶች  በቅርባቸው ሰው ወይም በትዳር አጋራቸው ህይወታቸው  እንደሚያልፍ ተነግሯል።

በኢትዮጵያ  የሚፈጸሙ ጥቃቶች ለሚመለከተው አካል ሪፖርት ስለማይደረግ እና ሴቶችም ሲደፈሩ በግዴታ እንዲያገቡ የሚደረጉበት ሁኔታ ሰፊ መሆኑ እና በተለያዩ ምክንያቶች የተረጋገጠ መረጃ ማግኘት እንዳይቻል እንቅፋት መሆኑን  በፕላን ኢትዮጵያ  የኮሙኒኬሽን ክፍል ሃላፊ የሆኑት ዶክተር ምስክር ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል ።

BisratNews

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ግዮን መጽሔት ዛሬ ቅዳሜ ግንቦት 1 2018 ዓ.ም ገበያ ላይ ውሏል !!!

በኢትዮጵያ ነፃ ኘሬስ ከ25 ዓመት በላይአገልግለናል !!! -የአርበኞች አደራና የትውልዱ...

ከሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ የተላለፈ ጥሪ

በክልላችን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እያደገ የመጣው የተሳሳተ ስሌት የወለደው...

በሆርሙዝ የባህር ወሽመጥ ላይ በከባድ መሳሪያዎች የታገዘ  የተኩስ ልውውጥ ተካሄደ

ለዓለም የንግድ ሰንሰለት እጅግ ስትራቴጂካዊ በሆነው የሆርሙዝ ባህረ ወሽመጥ...

የሲ.ኤን.ኤን መስራች ቴድ ተርነር ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

የዓለማችን ግዙፍ የዜና አውታር ሲኤንኤን መስራች ቴድ ተርነር በ87...