የሰነዶች ማረጋገጫ እና ምዝገባ አገልግሎት እንዳስታወቀው አንዳንድ ህገወጦች በምስሉ ላይ የሚታየውን የአየር መንገድውክልና እና መሰል ሃሰተኛ ሰነዶችን ከተቋሙ ተረጋግጦ የወጣ በማስመሰል ህብረተሰቡን በማጭበርበር የማይገባቸውን ጥቅም ለማግኘት እየሞከሩ መሆኑን ለተቋሙ በደረሰው ጥቆማ መረዳት መቻሉን አስታውቋል።
ተቋሙ እንዲህ አይነቱን የወንጀል ድርጊት እንደማይታገስ እና ተከታትሎ ለህግ እንደሚያቀርብ ያስታወቀ ሲሆን ህብረተሰቡም በእንደዚህ አይነት ሃሰተኛ ሰነድ እንዳይጭበረበርና መሰል አጠራጣሪ ሁኔታ ሲኖር ለፖሊስ ጥቆማ በመስጠት ወንጀል ፈፃሚዎች በህግ ተጠያቂ ሊያደርግ እንደሚገባ አሳስቧል።
የሰነዶች ማረጋገጫ እና ምዝገባ አገልግሎት የሚመነጩ የውክልና ሰነዶች ባር ኮድ ያላቸው ሲሆኑ ልዩ ውክልና ከሆነ ደግሞ የራሱ የሆነ መለያ ( security feature) እና ኤሌክትሮኒክስ/ደረቅ ማህተም የያዙ በመሆኑ በቀላሉ በሃሰተኛ መንገድ ሊዘጋጁ የማይችሉ መሆናቸውንም ተቋሙ አረጋግጧል።
