ህወሓት በሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ሂደት ላይ ያለውን ተቃውሞ ገለጸ

Date:

የሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ባወጣው ሳምንታዊ መግለጫ፣ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በትግራይ ስም እያካሄደ ያለውን ሂደት እንደማይቀበልና በሂደቱ የሚተላለፉ ውሳኔዎችም በትግራይ ህዝብ ላይ ተፈጻሚነት እንደማይኖራቸው አስታወቀ። ድርጅቱ በመግለጫው የትግራይ ህዝብ ጉዳይ በትግራይ ምድርና በራሱ በህዝቡ ብቻ ሊወሰን እንደሚገባ በአጽንኦት ገልጿል።

የኢትዮጵያ መንግስት በትግራይ ህዝብ ላይ የጀመረውን የህልውና አደጋ አጠናክሮ ቀጥሏል ሲል የከሰሰው ህወሓት፣ ይህንን ድርጊት ለመሸፈንና ለማደናገርም የትግራይ ህዝብ ሙሉ በሙሉ በተገለለበት ሁኔታ በተለያዩ ተቋማት አማካይነት የህዝቡን ሉዓላዊነት የሚጋፉ ውሳኔዎች እየተላለፉ መሆኑን ገልጿል።

በተለይም ከሰሞኑ በምክክር ኮሚሽኑ የተከናወነው ተግባር የትግራይ ህዝብ ተሳትፎና እውቅና የሌለው በመሆኑ ዛሬም ሆነ ነገ ተቀባይነት እንደማይኖረው ድርጅቱ አስገንዝቧል።

በተጨማሪም በመግለጫው ላይ እንደተመለከተው፣ ምክክር ኮሚሽኑ በትግራይ ስም ያካሄደው መድረክ ጥቂት “ለጊዜያዊ ጥቅም የተታለሉ” ግለሰቦችን የሰበሰበና የመንግስትን የፖለቲካ ፍላጎት ለማስፈጸም ያለመ ነው ብሎታል።

ትግራይ በምክክር ሂደቱ ላይ የማትሳተፍባቸው ምክንያቶች ለኮሚሽኑ ቀደም ብለው በግልጽ መነገራቸውን ያስታወሰው ህወሓት፣ ህዝቡ በአሁኑ ወቅት በረሃብና በበሽታ እየረገፈ ባለበት፣ መሬቱ በኃይል ተወሮ በሚገኝበትና የህልውና አደጋ ተጋርጦበት ባለበት ወቅት እንዲህ አይነት አጀንዳዎች ትርጉም የለሽ ናቸው ብሏል።

መንግስት የትግራይን ህዝብ ግልጽ ጥያቄዎች ወደ ጎን በመተው “ትግራይ በምክክር ሂደቱ መክራለች” የሚል የፕሮፓጋንዳ ስራ እየሰራ መሆኑን የጠቀሰው መግለጫው፣ ማንኛውም ወዳጅም ሆነ ጠላት የትግራይ ህዝብ ያልመከረባቸውና ያልተወከለባቸው ውሳኔዎች በምድር ላይ ተግባራዊ እንደማይሆኑ ሊያውቀው ይገባል ብሏል።


በመጨረሻም፣ የትግራይ ህዝብ ከመሰረታዊ የህልውና ጥያቄው ትኩረቱን የሚከፋፍሉ እንዲህ ያሉ “ተንኮሎችን” በመገንዘብ፣ ሉዓላዊነቱን ለማረጋገጥና ህልውናውን ለማስጠበቅ ከመቼውም ጊዜ በላይ ተደራጅቶ ትግሉን እንዲቀጥል ህወሓት ጥሪ አቅርቧል። 

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አክሊሉ ወንድሞቹ ለንባብ በቃ

በፀሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ የልጅነት ታሪክ ላይ ያተኮረ ለታዳጊዎች...

የኢራን ተፈጥሮአዊ ምሽጎች እና ስትራቴጂካዊ ጥበብ

​ግዮን መጽሔት :- በመካከለኛው ምስራቅ የጂኦ-ፖለቲካ ትኩሳት...

ለአድዋ ድል መታሰቢያ በአሜሪካ ቀን ተሰየመ

በአሜሪካ፣ የፔንሲልቪኒያ ግዛት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የአውሮፓዊያኑ 'መጋቢት...

ኢሎን መስክ የዓለማችን የመጀመሪያው ትሪሊዮነር ሆነ

ኢሎን መስክ የሀብት መጠኑ 1 ትሪሊዮን ዶላር ያለፈ የመጀመሪያው...