ሩሲያ የአፍሪካን ችግሮች በአፍሪካውያን የመፍታት መርህን እንደምትደግፍ ገለጸች

Date:

በአዲስ አበባ ጉብኝት እያደረጉ ያሉት የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ፣ አፍሪካ ለምትከተለው የመፍትሔ መርህ ድጋፋቸውን ገልጸዋል። ሚኒስትሩ በአፍሪካ ያሉ ግጭቶችን ለመፍታት አህጉሪቱ በራሷ አቅም መምራት እንዳለባት አስታውቀዋል።

ይህንን የገለጹት ከአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ማሃሙድ አሊ ዩሱፍ ጋር ምክክር ካካሄዱ በኋላ ነው።

ሩሲያ በሰሃራ-ሳህል ቀጠና እና በአፍሪካ ቀንድ የሚስተዋሉ ቀውሶችን በልዩ ትኩረት እንደምትከታተል ሚኒስትሩ ገልጸዋል።

በሱዳን፣ በደቡብ ሱዳንና በሊቢያ ያሉ አለመረጋጋቶች የሩሲያም አሳሳቢ አጀንዳዎች መሆናቸውን አረጋግጠዋል።

አፍሪካ የምትገጥማቸውን ፈተናዎች ለመፍታት የምታደርገውን ጥረት ሩሲያ እንደምትደግፍም ተናግረዋል።

“የአፍሪካ ችግሮች በአፍሪካውያን መፍትሔ” የሚለውን መርህ ሩሲያ በጽኑ እንደምትከተል ላቭሮቭ አስገንዝበዋል።

ሩሲያ አፍሪካን የምታግዘው ይህንን መርህ ባከበረ መልኩ ብቻ መሆኑን አክለዋል። ጉብኝቱ ሩሲያ ከአፍሪካ ሕብረት ጋር ያላትን ስትራቴጂካዊ ግንኙነት ለማጠናከር ያለመ ነው ተብሏል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከ12ኛ ክፍል ተፈታኞች  565 ትምህርት ቤቶች አንድም ተማሪ አላሳለፉም

በዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና በተመዘገበው ውጤት...

የአማርኛ ቋንቋ እውነተኛ ምንጭ ቤተ መንግሥት ሳይሆን ሕዝብና ሠራዊት ነው

በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የአማርኛ ቋንቋ ማበልጸጊያ ተቋም አዘጋጅነት ከስድስት...

አዲስ አበባ፦ የዜጎች ቀይ መስመር!

(የግል አስተያየት) አዲስ አበባ የኢትዮጵያውያን መናገሻ፣ የበርካታ ብሔረሰቦች ባህሎች ለዘመናት...

አብን የምክክሩን ውጤት ውድቅ አደረገ!

አብን በሀገራዊ ምክክሩ ማጠቃለያ ላይ የተፈጸመውን “ሕገ-ወጥ ጣልቃ-ገብነት” በመቃወም...