“ቅዱስነታቸው ምንም ያቀረቡት ጥያቄ የሌለ መሆኑን እንገልጻለን”

Date:

የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽሕፈት ቤት

“ከናፍረ ጻድቃን ያረትዓ ስምዐ፤ ወሰማዕት ጕጉእ ቦ ልሳን እኩይ፦ የጻድቃን ከንፈሮች ምስክርነትን ያቀናሉ፤ የሚቸኩል ምስክር ግን ክፉ አንደበት አለው።”

ከብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽሕፈት ቤት ወቅታዊ ጉዳዮችን አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ላለፉት ተከታታይ ዓመታት ወደ ሰሜን አሜሪካ በማምራት የሕክምና ክትትል ሲያደርጉ መቆየታቸው የሚታወቅ ሲሆን በቅርቡም ተመሳሳይ ጉዞ አድርገው ጳጉሜን 1 ቀን 2017 ዓመተ ምሕረት ወደ ሀገራቸው ኢትዮጵያ በታላቅ ክብር መመለሳቸው ይታወሳል።

ይህንንም ተከትሎ ርእሰ ዐውደ ዓመትን በማስመልከት ለመላው ኢትዮጵያውያን የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻቸው አባታዊ ቃለ በረከትና ቡራኬ በመገናኛ ብዙኃን አስተላልፈዋል፤ የመስቀል ደመራ በዓልንም በመስቀል አደባባይ ተገኝተው በማክበር ለመላው ሕዝበ ክርስቲያን አባታዊ ትምህርተ ወንጌል፣ ቃለ ምእዳንና ቡራኬ አስተላልፈዋል፤ ቤተ ክርስቲያናችን በየዕለቱ የምታከናውናቸው መንፈሳዊ፣ ማኅበራዊ እና ዓለም አቀፍ ተግባራትንም በጽሕፈት ቤታቸው ሆነው በአባትነት እየመሩ በተሟላ ጤንነት ላይ ይገኛሉ።

ይሁን እንጂ ድብቅ አጀንዳ ይዘው ሐሰተኛ መረጃን በማሰራጨት መደበኛውን የቤተ ክርስቲያን ሐዋርያዊ ተልእኮ ማደናቀፍ ዓላማቸው ያደረጉ አካላት በማኅበራዊ የትስስር ገጾቻቸው ባጋሩት ፍጹም ከእውነት የራቀ መረጃ ውሉደ ክህነት እና በጎ ሕሊና ያላቸው ምእመናን በእጅጉ መጨነቃቸውን ለመገንዘብ ችለናል።

ስለሆነም ቅዱስነታቸው ሐዋርያዊ ተግባራትን ለመምራትም ሆነ ለማከናወን የማያስችል ምንም ዓይነት የጤና እክል ያልገጠማቸው፤ ከዚሁ ጋር በተያያዘም ያቀረቡት ጥያቄ የሌለ መሆኑን እንገልጻለን።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!
አሜን።
መስከረም 28 ቀን 2018 ዓመተ ምሕረት
አዲስ አበባ ~ ኢትዮጵያ

©የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽ/ቤት

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የተፈናቀሉ ዜጎች በተጠለሉበት አካባቢ በቋሚነት መኖር የሚያስችላቸው 

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን የዳሰነች ወረዳ ከበኦሞ...

ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ 11ኛውን የኃይሌ ሆቴልና ሪዞርት በደብረ ብርሃን ከተማ አስመረቀ

ታዋቂው አትሌትና ባለሀብት ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ፣ በደብረ ብርሃን ከተማ...

በኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር የተዘጋጀው የመጀመሪያው አህጉራዊ የሪል ስቴት ኤግዘቢሽን ተከፈተ

በኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር አዘጋጅነት የመጀመሪያው አህጉራዊ የሪል...

በሊባኖስ እና በእሰራኤል የተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት ተራዘመ

ትራምፕ በሊባኖስ እና በእሰራኤል መካከል የተደረሰው የተኩስ አቁም በሦስት...