የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በ 2018 ዓ.ም ለሚያከናውነው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሲዳምኛ ቋንቋን ከመራጮች ምዝገባ እስከ ድምጽ አሰጣጥ ድረስ ባለው ሂደት ማካተቱን አስታውቋል።
አቶ መላከ አሉላ በቦርዱ የሎጀስቲክስ ክፍል ኃላፊ የምርጫ ቁሳቁስ እሸጋን አስመልክቶ ለጋዜጠኞች በሰጡት ማብራሪያ ቦርዱ ከዚህ ቀደም በአምስት ቋንቋዎች የምርጫ ሥርዓቱ ሲከናወን እንደነበር አንስተዋል።
ከዚህ ቀደም የክልሉን (ሲዳማ) ሪፍረንደም ሲካሄድ እንዲሁም 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ የተካሄደው በአማርኛ ቋንቋ መሆኑን አቶ መላኩ ገልጸዋል።
7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ቦርዱ የሲዳምኛ ቋንቋን በማካተት የምርጫ ሂደቱን በ6 ቋንቋዎች በማከናወን ላይ ይገኛል ተብሏል።
ቦርዱ ከዚህ ቀደም አማርኛ፣ አፋን ኦሮሞ ፣ ትግረኛ፣ ሶማሊኛና አፋርኛ የምርጫ ሂደቱን ሲያከናውን እንደነበር ይታወሳል።
